ኢትዮጵያዊነትን እያጥላሉ እና እያገለሉ  ኢትዮጵያ ማለት እንዴት ይሆናል ?

June 22, 2022

ኢትዮጵያዊነት በጠላትነት ተፈርጆ በህግ እና በፖለቲካ  አጥር ተከቦ የኢትዮጵያን አንድነት እና ህዝብ ደህንነት ጠንቅ ከሆነ ከሶስት አስርተ ዓመታት በላይ ዘመን አስቆጥሯል፡፡


ኢትዮጵያዊነት ከስሩ በመንቀል የኢትዮጵያን  አንድነት ለማዳካም የመጀመሪያዉ የጥፋት  ትልም ኢትዮጵያዉያንን -ዓማራ- ማታለል፣ ማጥላላት፣ ማግለል እና መግደል  ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያን የመጥላት ሰንኮፍ ከተተከለበት የጋራ የጥፋት ኃይሎች ስምምነት ከ1968 ዓ.ም. ስራ ላይ እንዲዉል የሆነዉ ፀረ ሴሜቴክ አጥፊ  ህገ – ክህደት እና ሞት ነዉ ፡፡

ከዚህ ፀረ ኢትዮጵያዊነት እና ፀረ- ሴሜቲክ  ምንጭ የተቀዳዉ የኢህዴግ /ህወኃት -ህገ- መንግስት እስካልቀረ ወይም እስካልተቀየር ድረስ ኢትዮጵያ እንደ አገር ዜጎችም እንደ ህዝብ በነፃነት  ህልዉናቸዉ ሊከበር ይችላል ብሎ ማሰብ ከድንቁርና በላይ ሞት ነዉ ፡፡

ለነፃነት እና ህልዉና ለማስከበር እና ለማንበር ብሎም ለማስቀጠል ከሌሎች ችሮታ መጠበቅ በድቅድቅ ጨለማ መሮጥ ነዉ ፡፡

ለነፃነት እና ለህልዉና የሚከከፈል ዋጋ ለባርነት እና ለሞት ከሚከፈል ዋጋ የላቀ መሆኑን በመረዳት በነፃነት እና በህልዉና መኖር ተፈሯዊ  መብት ምርጫ ሳይሆን ግዴታ መሆኑን በመገንዘብ ለማይቀረዉ ድል ራስን እና አገርን በአንድነት መከላከል ያስፈልጋል፡፡

ዓማራ ጠል አስተሳሰብ ሆነ ድርጊት ፀረ-ኢትዮጵያዊነት መሆኑን ላለፉት የጥልመት እና ሞት  ዓመታት በተግባር መታየቱን የሚያስተባብሉ እና የማይቀበሉ ሁሉ ፀረ-ኢትዮጵያ ከመሆን ሌላ ሊባል አይችልም፡፡

በኢትዮጵያዊነት እና  ማንነት ላይ የሆነዉ የዓመታት ዘር ፍጂት ()መካሄዱ እና ይህም በኢትዮጵ ታሪክ ሆኖ እና ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ኢትዮጵያዊነት (ዓማራነት) ጠላትነት ሆኖ መቀጠል ኢትዮጵያን እንደ አገር ለማስቀጠል ህልም እና ምኞት መሆኑን እየታወቀ  ከድርጊቱ ትክክለኛዉን ስያሜ አለመስጠት እና ዕዉቅና መንፈግ የአግላይ እና ገዳይ ትዕይንቱ እንዲቀጥል ሆኗል፡፡

ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ አስከ ዛሬ ዕለት በየትኛዉም ሁኔታ እና ምክነያት  በማንነታቸዉ እና ኢትዮጵያዊነታቸዉ  የዘር ፍጂት ሠለባ ለሆነዉ የዓማራ ህዝብ የሰማዕትነት መታሰቢያ እንዲኖር በማድረግ እንዲሁም ግንቦት ሀያ አስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት  ጀምሮ ብሄራዊ በዓል የድል ቀን መሆኑ ቀርቶ የጥልመት እና ሞት ቀን ሆኖ በየዓመቱ እንዲታሰብ ቢሆን ለጋራ ችግሮች የመፍትሄ ርምጃ ጅምር ይሆናል

ኔሎስ -አምበር

“ነፃነት እና ህልዉና ተፈጥሯዊ  እንጂ ችሮታ አይደለም ፡፡”

 

 

https://youtu.be/BSlbno_1ZnE

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ልበ ደንዳና፣ አንገተ ወፍራም መሪ ፕሮፋይል እና ከቨር ፎቶ መቀየር ውስጥ ይደበቃል – ዩሀንስ ሞላ

Next Story

ይህ ከአዲስ አበባ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ሙከ ጡሪ ውጫሌ ወረዳ ሰሜን ሸዋ ዞን ነው። ሸኔ አማራን ለማፅዳት በአብይ አህመድ የተመሰረተ ጦር

Go toTop