የጠቅላያችን ንግግር እና የአእምሮ ህመም ምልክቶቾ – የሽዋስ ዘወልድያ ሚካኤል (የስነ አእምሮ ባለሙያ)

June 16, 2022

ታንጀንሺአሊቲ (tangentiality) እና ሰርከምስቴንሻሊቲ (circumstantiality)

በስነ አእምሮ ህክምና በአእምሮ ህሙማን ዘንድ የሚነስተዋሉ የህመም ምልክቶች ናቸው ታንጀንሻሊቲ እና ሰርከምስቴንሻሊቲ

1.ታንጀንሻሊቲ(tangentiality)

የምንለው አንድ የአእምሮ ህመምተኛ ለተጠየቀው ጥያቄ ቀጥተኛ ያልሆነ ምላሽ ወይም ከጥያቄው ጋር የማይገናኝ ምላሽ ሲሰጥ ነው ከመጠን ያለፈ ወይም ተዛማጅነት የሌለው ዝርዝር ጉዳዮችን ሲዘረዝር ይውላል ወደ ነጥቡም ሊመለስ አይችልም

ለምሳሌ:- ስለ መንግስታዊ አፈና እና ስለ ህዝባዊ እንግልት ስትጠይቃቸው

መልሳቸው የሚሆነው ይኼን ያክል ኪሎ ሜትር አስፓልት ገንብተናል ስኳር ፋብሪካ ገንብተናል በአየር መንገዳችን 22 ቢሊየን ሰወችን አሳፍረናል ይኼን ያክል ችግኝ ተክለናል ይሆናል ይሆናል መቸም ቢሆን ግን ስለ አፈናው አይነግሩህም

እነዚህ ህሙማን ብዙ ቢያወሩም ወደ ተጠየቁት ጥያቄ አይመለሱም ለጥያቄውም መልስ ከወሬያቸው አታገኝም ይልቁንም ያልተባሉትን ሁሉ ያዘበዝቡልሀል ይተርኩልሀል

2.ሰርከምስቴንሻሊቲ (circumstantiality)

የምንለው ደግሞ አንድ የአእምሮ ታማሚ ለተጠየቀው ጥያቄ ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ዙሪያ ጥምጥም ይሽከረከራል ከንግግር ዋና ነጥብ የወጣ የወረዳ እና ቀጥተኛ ያልሆነ አስተሳሰብ ወይም ንግግር ያደርጋል፡፡ ይህንን ባህሪ የሚያሳየው ግለሰብ አላስፈላጊ እና እዚህ ግባ የማይባል መረጃን ያካትታል ቢሆንም ግን ከብዙ ዙሪያ ጥምጥም በኋላ መጨረሻ ላይ ወደ ዋናው ነጥብ ይመለሳል

ለምሳሌ ፋኖ ለምን ይሳደዳል በለህ ስትጠይቅ

ስለ ግብርና እና ስለማዳበሪያ ዋጋ ስለ ቡና ገበያ ስለ ድርድር ስለመከላከያ ጀግንነት እና ሌላም ሲያዘበዝብ ቆይቶ መጨረሻ ላይ ፋኖ የአማራም የኢትዮጵያም ኩራት ነው እንደማለት ነው

ብዙ ከጥያቄው ጋር የማይዛመዱ አላስፈላጊ ዝርዝሮችን ሲዘረዝር ውሎ መጨረሻ ላይ ወደ ነጥቡ ይመለሳል፡፡

እነዚህ ምልክቶቾ ብዙ ጊዜ የሚታዩት(schizophrenia and mood disorder with psychotic feature) በሚባሉ ህመሞች ነው

ትላንት በጠቅላያችን ንግግር ላይ የትኛውን አስተዋላችሁ አንደኛውን ወይስ ሁለተኛውን?

there is no health with out mental health

ያለ አእምሮ ጤና ጤና የለም

የሽዋስ ዘወልድያ ሚካኤል

(የስነ አእምሮ ባለሙያ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

“ስልጣን መጋራት ብቸኛው አማራጭ ነው ብሎ ከሚያስብ አጎብዳጅ ፓርቲ ጋር አባል ሆኜ መቀጠል አልፈልግም” – ክቡር ገና

Next Story

የኢዜማ ሚዛን ለባለቤቶቹ ትመለስ! – ከኡመር ሽፋው

Go toTop