በአማራ ክልል በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው ተገለፀ

June 8, 2022
 መንግስት የህግ ማስከበር ዘመቻ ብሎ በጠራው እና ከአራት ሳምንታት በፊት በጀመረው እንቅስቃሴ በአማራ ክልል በቁጥጥር ሰር ከዋሉት ውስጥ አብዛኛዎቹ እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ቤተሰቦቻቸው እና አንድ የሕግ ጠበቃ አስታውቀዋል ።
በክልሉ ለፍርድ ሳይቀርቡ እስከ 22 ቀን የሞላቸው ታሳሪዎች እንደሚገኙ የተጠርጣሪ ቤተሰቦች፣ የሥራ ባልደረቦች እና ጠበቆች ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣቸው መግለጫዎችም ሕጋዊ ያልሆኑ ያላቸውን አካሄዶች ተችቷል።
ሰሞኑን መግለጫ የሰጡት የአማራ ክልል መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በበኩላቸው የህግ ማስከበሩ እንቅስቃሴ ልዩ ዘመቻ በመሆኑ የፍትህ ሂደቱ ሊጓተት ይችላል ብለዋል።
የአማራ ክልል መንግሥት በክልሉ በፋኖ ስም ግድያ ፣ ዝርፊያ የሰዎች ዕገታ እና መስለ ሕገ ወጥ ወንጀሎችን በመፈፀም ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን ከ4ሺ 500 በላይ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ማስታወቁ ይታወሳል።
/ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ/VOA

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ዜጎች ከፍትህ ምንጭ ጠጥተው ይረኩ ዘንድ – ገለታው ዘለቀ

Next Story

ስለሀገር – “የመከላከያ አባላት ሚስቶች ናችሁ” በሚል ግፍ የተፈጸመባቸው የትግራይ ሴቶች አሳዛኝ ታሪክ

Go toTop