![](http://amharic-zehabesha.com/wp-content/uploads/2022/06/284594142_4980035762125997_4332042263139855699_n.jpg)
~ቀዳማዊ ኃይለስላሴን የተካው ደርግ በውስጡ የነበረው ሽኩቻ ገፍቶ ጥር 26፣1969
~ብ/ጄ ተፈሪ ባንቲን
~ሻምበል አለማየሁ ኃይሌን
~ሻምበል ሞገስ ወ/ሚካኤልን ጨምሮ 7 ጓዶቹ ላይ እርምጃ በመውሰድ አብዮታችን ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋግሯል የሚል መፈክር በማስተጋባት ኮሎኔል መንግሥቱ መሪነቱን መጨበጣቸውን አረጋገጠ።
ደርግን የተካው ህወሓት መራሹ ኢህአዴግ በ1993 ዓ ፣ም በገጠመው መሰንጠቅ አቶ ስዬን፣አቶ ተወልደን፣አቶ ገብሩን ፣ወ/ሪት አረጋሽን ጨምሮ የውቂያኖስ ሽንት እና ጃኬታቸውን አስወልቀን አባረርናቸው በሚል ፀያፍ ንግግር
አስወግዶ ሟቹ ጠ/ሚኒስትር ፍፁም ብቸኛ አምባገነን ሆነው ወጡ።
በዘመኑ የኮምፒውተር ቋንቋ ህወሓትን ሀክ አድርገው ስልጣን የቀሙት የኦሮሞ እና የአማራ ብልጽግናዎች መካከል በቀዳሚነት ከሚጠሩት አቶ ለማ ቀደም ብለው አቶ ገዱ ተከትለው ዛሬ ተሸኙ ። የእነዚ 3 ፎቶዎች ወግ ሲጠቃለል የታላቁን ባለቅኔ ከበደ ሚካኤልን ግጥም ያስታውሰኛል
ሺህ ዘመን ተጉዤ
ሺህ ዘመን ደርሼ
በሄድኩበት መንገድ
መጣሁ ተመልሼ
ተወልደ በየነ (ተቦርነ
ግንቦት 26 _2014 ዓ_ም
june 3 _2022