መስከረም አበራ ከኤርፖርት መታፈኗ ተሰማ

May 22, 2022

መንግስት እየሄደበት ያለው አካሄድ የፖለቲካ ቁርሾ ከመፍጠርና የሕዝብ አመፅ ወደ መቀስቀስ ነው። ወልዲያ እና ሌሎች የአማራ ከተሞች ላይ እየተደረገ ያለው ወታደራዊ ዘመቻም አሳሳቢ ነው። ባለፍነው እንዳልነው ሕዝብ ሰላም ይፈልጋል። አንድ ጊዜ በጦርነት ሌላ ጊዜ በአፈና እና በማሳደድ ሕዝብን ማሸበር የመንግስት ተግባር መሆን የለበትም ። የአማራ ኢሌቶችንና የአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪዎችን እየለቀሙ ማሰር ነገን ካለማሰብ ይመነጫል። ሕወሓትን በስልጣን ዘመኑ ይህን አይነት ድርጊት ይፈፅም ነበር፤ ሆኖም የሚፈፅመው ሰቆቃ በስልጣን እንዳይዘልቅ ሆኖ ተዋረደ። በጎንደር በጎጃም በወሎ በሸዋ በአዲስ አበባ እና በመተከል የሚደረኩ አፈናዎችና ሽብሮች ውጤታቸው አደገኛ እንዳይሆኑ አሁንም መንግስት ቆም ብሎ ሊያስብበት ይገባል። ሕዝብ መጨ`ቆን የመንግስትን ዱላ ሰልችቶታል። ሕዝብ ሰላም ይፈልጋል።

(ምንሊክ ሳልሳዊ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

 በአማራ ሕዝብ ላይ የሚካሄደውን ግፍና በደል በሚመለከት ከቪዥን ኢትዮጵያ የተሰጠ መግለጫ

Next Story

በሕግ ሥም አፈናው እና የጉዋዳ ድርድሩ የፈጠረው የኃይል አሰላለፍ

Go toTop