ከሩሲያ ጎን ሆነው በዩክሬኑ ጦርነት ለመሣተፍ ዛሬ በሩሲያ ኤምባሲ የተሰለፉ ወጣቶች

April 18, 2022
በወጣቶቹ ውስጥ የሚታየው የመጨረሻ አማራጫቸው ሄዶ ወይ መሞት ወይ መለወጥ ነው። በሃገርህና በመንግስትህ ተስፋ ስትቆርጥ እንኳን ይሄ ሌላም ይደረጋል። አይዞን ወገኔ!

እያደሩ ማነስ

በምስሉ ላይ የሚታዩት ኢትዮጵያውያን በሩስያ ኤምባሲ ደጅ የተሰለፉት ለሩስያ ለመዋጋት /ለመመዝገብ/ ነው እየተባለ ነው! ሩስያ በበኩሏ (ኤምባሲው ለአል አይን እንደገለጸው) ‘እኔ ወታደር እየመዘገብኩ አይደለም :ለእኛ ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት ነው የተሰበሰቡት ‘ብላለች! በሃገሪቷ ባለው የኢኮኖሚ ሁኔታ (ስራ አጥነት) እንኳንስ ሩስያ የትም ድረስ ለመሄድ የሚነሳ ወጣት መመልከት አይገርምም!
እየገረመኝ ያለው የመንግስት ነገር ነው።
በአለምአቀፍ ህግ ሰዎች ለሃገራቸው ካልሆነ በስተቀር ለሌላ ሃገር ተቀጥረው መዋጋት አይችሉም!(መርሲናሪዝም በየትኛውም ቦታ የተወገዘ ነው) ኢትዮጵያ ራሷ ፈራሚ በሆነችበት ‘መርሲናሪዝምን ከአፍሪካ ምድር ለማስወገድ የተደረገ ስምምነት’ (ሊብረቪል 1977) ሃገራት ዜጎቻቸው ለሌላ ሃገር ተቀጥረው እንዳይዋጉ የሚችሉትን ሁሉ ማድረግ እንዳለባቸው የተደነገገ ሲሆን በዚሁ ስምምነት አንቀጽ 7 ላይ ፈራሚ ሃገራት ይህን ድርጊት በሃገራቸው የውስጥ ህግ ‘እስከ ሞት ድረስ የሚያስቀጣ ወንጀል ‘ ማድረግ እንዳለባቸው ይገልጻል!
እንግዲህ ኢትዮጵያም በዚሁ ተስማምታ ፈርማለች ።መፈረምም ብቻ ሳይሆን እኤአ በ1982 በሃገር ውስጥ አጽድቃለች! ይህን በፎቶው ላይ የሚታየውን ድርጊት አንዳንዶች ሊዘባበቱበት ቢችሉም የጸጥታ አካላት ግን ዝም ብሎ ማየት የለባቸውም! በአንድ ወቅት በአፍሪካም ሆነ በአለም አለም አቀፍ ህግን በማስከበርም ሆነ በማክበር ምሳሌ በነበረች ሃገር ይህን አይነቱን ነገር ማየት ያማል!
እስከአሁን ባለማወቅ ዝም ተብሎ እንኳን ቢሆን ከነገ ጀምሮ ግን ይህን አይነቱ ነገር ሊቆም ይገባል!

Andualem Buketo FB የተገኘ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

በጦርነትና ግጭት ውስጥ ሆነው የተፈተኑና የማለፊያ ነጥብ ያላመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ2014 ዓ.ም መደበኛ ተፈታኞች ጋር እንዲፈተኑ ውሳኔ ተላለፈ

Next Story

አቢቹ ፦ ነቄ ተብለሀል! (እውነቱ ቢሆን)

Go toTop