ዛሬ እለተ ማክሰኞ ከምሽቱ 3:30 አከባቢ ከሻሸመኔ ወደ ሀዋሳ በአንድ ቪትዝ መኪና አምስት ሆነን እየሄድን ነበር። ከፊት ለፊታችን አንድ ዶልፊን ሚኒባስ ከርቀት ይታየናል።
ከሻሸመኔ ወደ ሀዋሳ መሄጃ መንገድ ከሻሸመኔ ወጣ እንዳልን በተለምዶ ቻይና ካምፕ የሚባል ቦታ ገመድ ተወጥሮ ለፍተሻ እንድንቆም ታዘዝን፣ ፈታሾች መጥተው ፈትሸው አሳለፊን ከነሱ በግምት 300 ሜትር ርቀት ላይ እንደገና ሌሎች ፈታሾች መንገድ ዘግተው አስቆሙን ። እነዚህኛዎቹ የመከላከያ ልብስ የለበሱ፣ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ልብስ የለበሱ ፣ አንፀባራቂ ጃኬት የደረቡ ፣ በአግባቡ ባትሪ ይዘው መሳሪያ ታጥቀው የቆሙ ናቸው።
ቁሙ ሲሉን ቆምን ከዛም ለፍተሻ ውረዱ ብለው አስወረዱን መኪናዋን ገልብጠው ፈተሹ የሚጠቅም የማይጠቅም ነገር ሁሉ ከመኪናዋ አወጡ ፣ እኛን አሰልፈው መፈተሽ ጀመሩ ፣ ስልካችንን ከሁላችንም ላይ ተቀበሉ። ኪሳችንን ገልብጠው ያለንን በርካታ ገንዘብ ወሰዱ ፣ ከአንገታችን ብርና ወርቅ አስወለቁ።
ከዛ ክላሻቸውን ወደኛ ወድረው በማቀባበል በያዙት ዱላ ይቀጠቅጡን ጀመር። የሚናገሩትን ቋንቋ እየተናገርን ሊሰሙን አልፈለጉም እየቀጠቀጡ ወደ መኪና አስገብተው መሳሪያ በማቀባበል ቀጥ ብላችሁ ሂዱ ብለው አስገደዱን።
በሀገራችን፣ በትውልድ መንደራችን ፣ በመኖሪያ ቀያችን ተዘረፍን
ህጋዊ አካል ናቸው ብለን ተገደልን፣ተደበደብን
መንግስት በየሰፈሩ ገመድ እየወጠረ በፍተሻ ሰበብ ጥሪታችንን አስነጠቀን
ሻሸመኔ እንዲህ አደረገችን ደራሽ አጣን ፣ ሀገር አጣን
እኔም በደረሰብኝ ድብደባ ለጉዳት ብዳረግም የተዘረፍኩት ሳይሆን ያጣዋት ሀገሬን፣ የጠላዋት መንደሬን እታሰብኩ ይህንን ፃፍኩ።
ወገኖቼ ዋስትና የለንም
በቃ እራሳችንን እንጠብቅ፣ በጊዜ እንሰብሰብ
የሻሸመኔ የሚመለከታቸው አካላት
የፌደራል የሚመለከታቸው አካላት
ምላሽ ይስጡ አጋሩልኝ
Yerassew gezahagn