ታጣቂዎቹ የእኔ ናቸው ካለ ከአማፂያን ጋር ይሰራል ማለት ነው?
በክልሉ ከዚህ ቀደም በፒክ አፕ የተጫኑ የፌደራል ፖሊስ አባላት እና የኦሮምያ ክልል ልዩ ሃይል አባላት በሸኔ ሲገደሉ ሃዘን ያልተሰማው ዛሬ እንዴት ተሰማው?
በርካታ ዜጎች ሲገደሉ ትንፍሽ ሳይል ትላንት ስለምን ጥልቅ ሀዘን ውስጥ ገባ?
መግለጫውን ለማውጣት እጅግ በጣም የፈጠነበት ምክንያትስ ቀድሞ ስክሪፕቱ ስለተፃፈ ይሆን?
የክልሉ መግለጫ ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መግለጫ ጋር እንዴት አልጣጣም አለ?
ክልሉ የፀጥታ ሃይሎቼ ተጎዱ ካለ የአንድ ክልል ልዩ ሃይል ሌላ ክልል ውስጥ እንዴት ሊገባ ቻለ?
ለማንኛውም የአማራና የኦሮሞ ህዝብ በእናንተ ተራ ሴራ እግር ስር አይወድቅም። ከፍተኛ የስራ ልምድ ያለው ህወሃትም አልቻለ። ህዝቡን ረፍት ስጡት ማለት ዛሬ ነው።
በነገራችን ላይ ይህ ጉዳይ በቀላሉ መታየት የለበትም። ህዝብን ከምታደናግሩ አጣርታችሁ በግልፅ የተፈጠረውን ለህዝብ ይፋ አድርጉ።