ኢትዮጲያውያን ትኩረታቸውን ወደ ዋግ ምድር ያድርጉ
መንግስትና የረድኤት ተቋማት በሚቻለው ሁሉ ፍጥነት ችግሩ ተባብሶ ሳይቀጥል ርብርብ ሊያደርጉ ይገባል
ቀጣዩ ዘገባ የዋግ ኮሚኒኬሽን ነው
በዝቋላ ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች እጣ ፈንታ እንዲህ ሆኗል!:: ይህ ህጻን ምስጋናው አይናለም ይባላል በዝቋላ ወረዳ ዘራፊው የትሄነግ ቡድን በያዘባቸው ቅዳሚት አከባቢ 06 ርዕሰ ገነት ቀበሌ ልዩ ቦታ አልቆዙ ከምትባል ጎጥ የመጣ ነው። ሁለት ሶስት ህጻናት አቅፋና ያዘለች እናት እንዴት ታጥግባቸው፤ እንዴትስ ብላ ትታደጋቸው፤ ለራሷ የምትልሰው የምትቀምሰው የሌላት፣ እንዴት ወተት ታመነጭ፤ ህጻኑ የናቱን የጠወለገ፣የጠነዘለ ባዶ ቁርበት ጡት ቢጎት እንዴት ወተት ይውጣ!
በዝቋላ ወረዳ ጽጽቃ ጤና ጣብያ ይህ ህጻን ብቻ አይደለም፣ ሌሎች ያልጋ ቁራኛ የህኑ ህጻናትና እናቶች እንዳሉ የዝቋላ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጸ/ቤት ተወካይ ሀላፊ አቶ እስጢፋኖስ ወንዳያ ተናግረዋል። ዋግ አሁንም ደራሽ ወገን ትሻለች፣ የሚታደጋት መንግስት ትማጸናለች፤ እነዚህ ተፈናቃዮች የእለት ጉርሳቸውን ከማግኘት የዘለለ ከወራሪው የትህነግ ቡድን ተደምስሶ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የዘወትር ጥያቂያቸው ሆኗል።
እንደ ተወካይ ሀላፊው ገለጻ በጽጽቃ ጤና ጣብያ የተኙ ህጻናትና እናቶች እንደ አብነት አነሳን እንጂ ከጤና ጣብያዎቻችን አቅም በላይ የሆኑ ተፈናቃዮች እናቶችና ህጻናት በርካታ ናቸው ብለዋል።
ዛሬም ዋይ ዋይ እያሉ ነው፤ ዛሬም ነፍስ አድን ሰው ፍለጋ ላይ ናቸው። የዝቋላ ወረዳ ነዋሪች እንደተናገሩት ችግራችን የሚፈታው በወራሪው የተያዘው ቤታችን፤ የተቀማው ንብረታችን ሲመለስ፣ በዬ በረሀው ተበታትነው የሚታረዱ ፍየሎቻችንና ከብቶቻችን ወደ በረታቸው ሲመለሱ ነው በማለት ለሚመለከተው ሁሉ ይማጸናሉ።
ወሎ ኅብረት