![](https://amharic.thehabesha.com/wp-content/uploads/2022/03/275751643_3150703011914168_2960228920287557200_n.jpg)
የተከበራችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን በየአላችሁበት የከበረ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ!
* * * *
ጁንታው ኢትዮጵያን ለመበታተን የአማራን ህዝብ ዘሩን ለማጥፋት አላማ አድርጎ ወረራ በጀመረበት ወቅት፤ እኔም እንደ አንድ ዜጋ ለሀገሬና ለህዝቤ የሚጠበቅብኝን ለማድረግ ቀን ከሌሊት ያለ ድካም በትግሉ ጎራ ከተሰለፉት የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ሀይሎች፣ ሚሊሻና የአማራ ፋኖ እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ በሚያደርግበት ጊዜ እኔም ህዝቤን በመሰብሰብ የሞራል ግምባታን ስሰጥ፣ ያለኝን ሁሉ ያለ ስስት ሳበረክት ቆይቻለሁ።
ይሁንና ወራሪው ሀይል በአማራ ክልል ዘልቆ ጥፋትና ውድመት እየፈጸመ በመጣ ጊዜ “ሊበላህ የመጣውን ጅብ በልተኸው ተቀደስ” በሚል የአባቶቼ ብሒል በመነሳት ልዩ ስፍራው በጎጃም መርጡ ለማርያም አካባቢ ሚሊሻውን ሰብስቤ በማነጋግርበት ወቅት ወራሪው ጠላት ሀገርን ለብተና አማራን ጨርሶ ለማጥፋት በከፍተኛ ፍጥነት እየገሰገሰ መምጣቱን አስመልክቶ፤ ጨርሶ ሊያጠፋን የመጣውን ጠላት በማንኛውም መልኩ እስከ ህይዎት ፍጻሜ እንድንዋጋው ለማስገንዘብ የተናገርኳቸውን ንግግሮች በከፊል ቀነጫጭበው ከዋናው አውድ በራቀ መልኩ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨትና በኔ ላይም ያልተገባ የታሪክ ስሁት ለማስረጽ ወርቁ አይተነው “እንደ ፍዬል ጠብሳችሁ ብሉት” ብሏል በማለት ጥቂቷን ንግግር ለብቻ በመቀንጨብ የሰውን ልጅ አርዶ ስለመብላት ያስተማርኩና የሰበኩ አስመስለው ያወጡት ቪዲዮ ለሰፊው ህዝብ ለምወዳችሁና ለምትወዱኝ ወገኖቼ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ሙሉ ንግግሬን ከታች ያስቀመጥኩ በመሆኑ የጠላትን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ስራና፤ በኔ ላይም የሚደረገውን የስም ማጥፋት ዘመቻ፣ ከዚያም አለፍ ብሎ ከአባት አያቶቼ ያልተማርኩትን አረመኔአዊነት የተላበስኩ አስመስለው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያሰራጩት ቪዲዮ አውዱን የሳተ መሆኑን እንድትረዱልኝ ስል በአክብሮት እጠይቃለሁ።
ይህም ወራሪው ሀይል ህዝብን የማይወክል የተገነጠለ ጁንታ ሲሆን በህዝብ ለይ የፈጸማቸው ግፎች ቀላል የማይባሉ ታሪክ መዝግቦ ያስቀመጣቸው በደሎች በርካታ ናቸው።
ከእነሱም መካከ፦ ባልን አስቀምጦ ሚስቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ደፍሯል፣ ገና ምንም ያላወቁ ጨቅላ ህጻናትንና መነኮሳትን ከገዳም እያወጣ ሲደፍር የነበረ ጨካኝ ሀይል ነበረ።
ይሄን ጭካኔ የፈጸመን ሀይል መታኮስና ፊለፊት መጋፈጥ ሳይሆን በፉጭራም ሆነ እንደፍየል ጠብሶ መብላት ነው ብሎ ለልዩ ሀይላችንና ለሚኒሻችን ለፋኖዎቻችን ጁንታው በህዝባችን ለይ ሲፈጽም የነበረውን ከፍተኛ የጭካኔ ድርጊት ተንተርሰን ሁኔታው የከፋ መሆኑን የተጠቀምንበትን ቃል እነ ቆርጦ ቀጥል ዛሬ እንደ አዲስ እየቆራረጡ ሁኔታው ወደሌላ የሄደ በማስመሠል ላይ ይገኛሉ።
![](https://amharic.thehabesha.com/wp-content/uploads/2022/03/275747670_3150703128580823_7095846210162661297_n.jpg)
አሁንም ይህ ወራሪ ሀይል በአማራ ክልል ለይ ግፍ ለመፈጸም ያቀዳቸው ብዙ አስከፊ ነገሮችና ሌላ ችግር ለመፍጠር ብሎም የጭካኔ ስሜት ለማድረግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ለይ እንዳለ ይታወቃል።
ለምሳሌ የተለያዩ አጀንዳዎች በመስጠት እኛ በእዚህ አጀንዳ ስንሻኮት እሱ የራሱን ስራ ለመስራት ስለሆነ ይሄ ታምኖበት ከእውነት የራቀውን ውሸት ከቁም ነገር በለመቁጠር ወደ ዋናው ትኩረታችን ሄደን በክልላችን ሳንበታተን አንድ ሆነን ፣ በአንድ አስበን ፣በጥቅሻ ተግባብተን በእዚህ ወራሪ ሀይል ለዳግም ጥቃት እንዳንዳረግ አጀንዳችንን ና የአጀንዳ ማስጠያ ቃሎችን በአጠቃላይ በደላሎቻቸውና በተከፋይ ዩቲዩበሮቻቸው የሚያደርጉትን የሳይበር ጦርነት ወደ ጎን አሽቀንጥረን በመተው ዝግጅት እናድርግ።
ሀገራችን ለሁላችንም ትበቃለች። የመልማት ጸጋዋን ተጠቅመን በፍቅርና በአንድነት ተሳስበን እጅ ለእጅ ተያይዘን ለሁለንተናዊ እድገት ራሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ። ከዚሁ በተቃራኒ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሀሰት ታሪኮችን እውነት በማስመሰል እየተወኑ ያሉት ሀገር አፍራሽ ሀይሎች ስንቃቸው ውሸት ጥይታቸው ቅጥፈት ስለሆነ የሚሰጡትን አጀንዳ ወደ ጎን በመተው በራሳችን አጀንዳዎች ዙሪያ በርትተን እንድንሰራ ስል በአክብሮት እጠቃለሁ።