የአቶ ፀጋ አራጌ ውሳኔ የሕዝብ መነጋገሪያ ሆነ -ያሬድ መኮነን

February 12, 2022
አቶ ፀጋ አራጌ

አቶ ፀጋ አራጌ የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሲሆኑ አቶ ደመቀ መኮንን በሚመራው ስብሰባ ላይ በአማራ ህዝብ ላይ እየተካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ ጅምላ ጭፍጨፋ አውግዘው የአማራ ባለስልጣናት ከፍርሃት እና አድርባይነት እንዲወጡና ህዝባቸውን እንዲታደጉ ጠይቀዋል።

አቶ ፀጋ አራጌ “በፓርቲያችን ብልጽግና ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የህግ ጥሰትና የአሰራር መዛነፍ እንዲስተካከል ስለመጠየቅ” በሚል ርዕስ ለፓርቲው የቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን በቀጥታ፣ በግልባጭ ለፓርቲው ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ደብዳቤያቸውን ማስገባታቸው ታውቋል።

አቶ ጸጋ አራጌ ለኦዲት ኮሚሽን ያቀረቡት ደብዳቤ የተለያዩ የህግ ጥሰቶችን የሚያነሳ መሆኑንም ተመልክቷል። በተለይም የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ በደንቡ የተሰጠው ስልጣንና ተግባር አካሉ ሳያውቀው ሙሉ ለሙሉ መጣሱን አመልክተዋል። ማዕካላዊ ኮሚቴው ማንም አካል በማያውቀው መንገድ ሁለት መደበኛ ስብሰባ አልፎበት ሶስተኛው መደበኛ ስብሰባን ለማሳለፍ በመንደርደር ላይ መሆኑንም አሳውቀዋል።

በአንጻሩ የፓርቲው ፕሬዝዳንት አብይ አህመድ የፓርቲውን ከፍተኛ የስልጣን አካል የሆነውን የፓርቲ ተቋም የማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባን በማጠፍና በመተው በህግም፣ በአሰራርም ሆነ በሞራል የማይመለከታቸውን ኢመደበኛ አደረጃጀቶችን በመሰብሰብ የፓርቲውን የፖለቲካና የትግል መድረክ ሆን ብለው የማቀጨጭ አቅጣጫ ተከትለዋል ይላሉ። ይሄም የፓርቲውን ቁመና በእጅጉ ጎድቶታል በማለት አቶ ጸጋ አራጌ ይከሳሉ።

የፓርቲው ጉባኤ በሁለት አመት ተኩል መካሄድ እንዳለበት በህግ ቢቀመጥም ማዕከላዊ ኮሚቴው በማያውቀው ሁኔታ ለሶስት አመት ተኩል እንዲራዘም ተደርጓል ይላሉ። በአሁን ሰአት ደግሞ ማዕከላዊ ኮሚቴው ለማንኛውም አካል ውክልና ባልሰጠበት ሁኔታ ህገወጥ አዘጋጅ ኮሚቴ በማን እንደተቋቋመ የማይታወቅ የጉባኤ ዝግጅትን እየመራ ማዕከላዊ ኮሚቴው እንደ አካል የማያውቀውን ሰነድ ቀጥሎ ላሉ የመዋቅር አባላት እያወረደ በማደናገር ላይ ነው ሲሉም ይከሳሉ።

በፓርቲው ውስጥ ዲሞክራሲያዊ አሰራር እየቀረ በጸረ ዲሞክራሲያዊ አሰራር እየተተካ ነው ይላሉ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ጸጋ አራጌ። ሁሉም ነገር በግለሰብ የግል ፍላጎትና በተናጠላዊ እንቅስቃሴ እየተሰራ በመሆኑ ፓርቲው የግለሰብ ተንቀሳቃሽ ንብረት እስኪመስል ድረስ ተቋማዊ ህልውናውን እስከማጣት ሊደርስ የሚያስችል የህልውና አደጋ ተደቅኖበታል ብለዋል።

የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉ አቶ ጸጋ አራጌ የቁጥጥርና የኢንስፔክሽን ኮሚሽኑ በ48 ሰአታት ውስጥ የጽሁፍ ምላሽ የማይሰጣቸው ከሆነ ፓርቲዎችን ለማስተዳደር ስልጣን ለተሰጠው ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለማቅረብ የሚገደዱ መሆኑን በደብዳቤያቸው ላይ አሳውቀዋል።


አቶ ፀጋ አራጌ ባለስድስት ገጽ ደብዳቤ ውስጥ ከሰፈረው ቁም ነገር ውስጥ አንዱ የብልጽግና ፓርቲ የገንዘብ መዝረፊያና መባከኛ ሁኔታን ከገለጹበት ማስረጃ ውስጥ ፓርቲው ለምርጫው ብሎ ከበጀተው ገንዘብ ውስጥ 60 ሚሊዮን ብር የብአዴን 12 ከፈተኛ አመራሮች ተከፋፍለውታል በማለት በድፍኑ ካሰፈሩ በኋላ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ደግሞ ያለአግባብ እንዲባክን ተደርጓል በማለት በፓርቲው ውስጥ የሰፈነውን አይን ያወጣ ዘረፋን አስቀምጠዋል።

ሽጉጥ እጠጣለሁ ብሎ የፎከረው እና 9 ሚሊዮን ብር ለግል ጥቅሙ ያዋለው አቶ አገኘሁ ተሻገር ህወሀት ወደ አራት ኪሎ ልትመጣ ነው በሚል ፍርሃት የተከፋፈሉት 60 ሚሊዮኑን የተቀራመቱት 12ቱ የብአዴን ባለስልጣናት ዝርዝር

1ኛ – አገኘሁ ተሻገር -9 ሚሊዮን ብር

2ኛ- አብርሃም አለልኝ – 8 ሚሊዮን ብር

3ኛ- ደሳለኝ በላይ- የፓርቲ ዘርፍ ኋላፊ – 8 ሚሊዮን ብር

4ኛ – ጎሹ እንዳለማው የብልጽግና ኋላፊ -8 ሚሊዮን ብር

5ኛ ጌትነት የብልጽግና ፋይናንስ ኋላፊ – 8 ሚሊዮን ብር

6ኛ – ፍስሀ ደሳለኝ -4.9 ሚሊዮን ብር

7ኛ – አማኑኤል የወጣቶችና ስፖርት ዘርፍ ኃላፊ -4.9 ሚሊዮን ብር

8ኛ – የብልጽግና አደረጃጀት ዘርፍ ኋላፊ – 4.9 ሚሊዮን ብር

9ኛ – ጥላሁን የብልጽግና አደረጃጀት ምክትል ኃላፊ -1.5 ሚሊዮን ብር

10ኛ – ፍቃዱ ዳምጤ የብልጽግና ኦዴትና ቁጥጥር ዘርፍ ኋላፊ -1.5 ሚሊዮን ብር

11ኛ – ባህሩ የብልጽግና አደረጃጀት ምክትል ኋላፊ 1.5 ሚሊዮን ብር

12ኛ – ደሳለኝ የፖለቲካ ዘርፍ ኋላፊ -1.3 ሚሊዮን ብር

እናመሰግናለን ቆራጡ አቶ ፀጋዬ አራጌ

( ምንጭ : አሻራ ሚዲያ )

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የምክር ቤት ውሎ ትዝብቶቼና መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች – በዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ

Next Story

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በወቅታዊ ሀገራዊና ድርጅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን አሳለፈ

Go toTop