ቤቴ ድረስ መጥተው አስፈራሩኝ – አስቴር በዳኔ ዘ-ኢትዮጵያ

February 3, 2022
አስቴር በዳኔ ዘ-ኢትዮጵያ

ሰላም ለእናንተ ይሁን

ቤቴ ድረስ መጥተው አስፈራሩኝ።

ለፖሊስ አሳውቄ አሁን ፖሊሶች ጥበቃ እያደረጉልኝ ነው።

ሁኔታው እንዲህ ነው።

ሰሞኑን በሰጠሁት ኢንተርቪው ሳቢያ ብዙ ነገር እየተባለ ነው።

እኔ የማንንም ብሔር አልተናገርኩም። በአዲስ አበባ ውስጥ ከእለት እለት የሚፈጸሙ ህገወጥ ድርጊቶች ስጋት ስለሆኑ የሚመለከተው አካል እንዲያስብበት አስተያየት ሰጥቻለሁ።

በወቅቱ የደረሰብኝ ነገር አስቆጥቶኝ የሰነዘርኳቸው ቃላት ለወንጀለኞች እንጂ ማንንም የህብረተሰብ ክፍል የማይወክል መሆኑ ይታወቃል። ድጋሚ ልብ ብላችሁ ብታዳምጡት አሁን በማስፈራራት ለምታሸብሩኝም ሰዎች ጭምር የሚጠቅም ንግግር ነው የተናገርኩት።

አሁን ቤቴ ድረስ መጥተውም ሊያስፈራሩኝ የሞከሩት ሰዎች አንድን ማህበረሰብ ነክታለች ብለው እየወነጀሉኝ ነው።

ከዚህ በፊት “የአዲስ አበባ ልጆች የ… ልጆች ናቸው” ብሎ ለተናገረው ሰው ነው ኃይለ ቃል የተጠቀምኩት።

አሁንም ቢሆን ባለመረዳት የተናገርኳችሁ የመሰላችሁን ሰዎች ይቅርታ እጠይቃለሁ።

ሀገሩ ሰፊ ነው ለሁላችንም ይበቃል። ትናንሽ ነገሮችን እያጋነንን ለግጭትና ለብጥብጥ መንስኤ አናድርጋቸው።

እኔ የማንም ወገን ሳልሆን የእውነትና የፍትህ ድምፅ ለመሆን ነው ዘመኔን ሁሉ የገፋሁት።

ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ችግር ቢገጥማት ድምፅ ሆኛታለሁ፤ ለታሰሩ ለተጨቆኑ ድምፅ ሆኛለሁ። በኔ ምክንያት ምንም ችግርና ብጥብጥ እንዲነሳ ስለማልፈልግ እንድረስልሽ ያሉኝን የኢትዮጵያ ወዳጅ ወጣቶች እንዳትመጡ ፖሊስ ጥበቃ ያደርግልኛል ብዬ መልሻቸዋለሁ።

ጉዳዩን ግን ማንኛውም ሀገር ወዳድ ዜጋ ማወቅ ስላለበት በዚህ ገጼ ላይ ለመፃፍ ተገድጃለሁ።

እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን።

አስቴር በዳኔ ዘ-ኢትዮጵያ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የኤርትራው የደህንነት ክንፍ ያወጣው መረጃ ነው ። እንዲህ ተተርጉሟል

Next Story

ግድፈቶችን በውስጣዊ ሥርዓት በማረምና አንድነታችንን በመጠበቅ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት ኢዜማዊ ማህትማችንን ማሳረፋችንን እንቀጥላልን!

Go toTop