ፋኖ ትጥቅ ይፍታ የሚልህን “ቀልቀሎ ስልቻ ስልቻ ቀልቀሎ” በለው – ዮሐንስ ቧያለው

January 14, 2022
ፋኖ የአማራ ህዝብ የተደቀነበትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በሬ ሽጦ ነፍጥ ያነሳ ከህዝብ አብራክ የተፈጠረ አራሽ፤ ተኳሽ፤ ቀዳሽ የነፃነት ታጋይ ነው። በአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነው የህልውና ጠንቅ ሲቀለበስ ፋኖ ነፍጠኛው ሰላማዊ ህዝብ ሆኖ ይኖራል።
NB፦ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ።
———————-
መንግሥት ፋኖን ትጥቅ ሊያስፈታ ነው የሚለው አሉባልታ መሰረተቢስና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ የጠላት ሴራ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ።
መንግሥት ፋኖን ትጥቅ ሊያስፈታ ነው የሚለው አሉባልታ መሰረተቢስና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ የጠላት ሴራ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት አስታውቋል።
የክልሉ መንግሥት ከፋኖ አደረጃጀት አባላት ጋር ተወያይቷል።
ፋኖ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሀገርና ሕዝብን እየታደገ ያለ መከታ ኃይል ነው። ስለሆነም የፌደራልም ኾነ የክልል መንግሥት ፋኖን ትጥቅ የማስፈታት ሐሳብ የለውም፤ ሊኖረውም አይችልም ተብሏል በመድረኩ።
በቀጣይ የክልሉ መንግሥት የመሳሪያ አስተዳደር ሥርዓቱን ሊያሻሽል እንደሚችልም ተገልጿል።
ፋኖ በስምም ሆነ በግብሩ የአማራ ሕዝብ ክብር መገለጫ በመሆኑ በፋኖ ስም የሚነግዱ አካላትን ፋኖና መንግሥት በጋራ ይታገላሉ ተብሏል። ፋኖን ማደራጀትና ማጠናከር የክልሉ መንግሥት አቅጣጫና ተግባር ኾኖ ሳለ ትጥቅ ማስፈታት የሚለው አሉባልታ አማራን የመከፋፈል እርስ በርስ የማጋጨት የማዳከም ሴራ አካል መሆኑም ተገልጿል ሲል አሚኮ ዘግቧል።
አሚኮ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

aklog birara 1
Previous Story

የሽብርተኛ አዋጅ ደንግጎ ሽብርተኛን መፍታት ሊያመጣ የሚችለው ክስተት ምን ይሆናል?

Next Story

ከላይ ሆነን ስናይ – ገለታው ዘለቀ

Go toTop