ተማሪዎች እና መምህራን በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ ሲሳተፉ ውለዋል

December 7, 2021
ለአንድ ሳምንት መደበኛ ትምህርት መቋረጡን ተከትሎ በተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎች እና መምህራን በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ::
በዛሬው እለት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ ተማሪዎች እና መምህራን ሰብል በመሰብሰብ፣ ደም በመለገስ እና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶችን ሲያከናውኑ ውለዋል፡፡
የሁሉተኛ ደረጃ ትምህርት መዘጋቱን ተከትሎ የተለያዩ መርሃግብሮች ተዘጋጅተው እየተከናወኑ ሲሆን ሰብል መሰብስብ፣ ድጋፍ ማሰባሰብ፣ የዘማች ቤተሰቦችን ማገዝ እና ደም መለገስ የመርሀ ግብሩ አካላቶች ናቸው።
መርሃ ግብሩም እስከ አርብ ድረስ በተለያዩ አገልግሎቶች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ዲያስፖራ ሆይ! ዘራፊዎች እንደገና ሊያፈርሱት ተሚችሉት ጎጆ በፊት ፋኖን ገንባ!

Next Story

ዘግይቶ ባገኘነው ዜና: ለቸኮለ! ማክሰኞ ኅዳር 28/2014 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

Go toTop