አስቸኳይ መግለጫ ከአማራ ህዝባዊ ሰራዊት (ፋኖ)

November 10, 2021
በዛሬው ዕለት ከተወሰኑ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረግነው ውይይት ወደ ውጊያ መግባት ስለምንችልበት እና ህዝቡን ለህልውና ዘመቻው በጋራ ስለምንቀሰቅስበት ሁኔታ መግባባት ላይ ደርሰናል!
መንግስት ያደረገውን የመጀመሪያውን የክተት ጥሪ ተከትሎ የተመሰረተው የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶችን ሲያደራጅ፣ ሲያነቃ እና ሲያሰለጥን ቆይቷል። በቅርቡም ወደ ግምባር ለማምራት በርካታ ፋኖወችን ካምፕ አስባስበን ለውጊያ ዝግጁ ብናደርግም በወቅቱ በገለፅነው ችግር ምክንያት ፋኖዎችን ወደየ ቀያቸው ተመልሰው ራሳቸውን በትጥቅ እንዲያዘጋጁ ለማድረግ ተሞክሯል።
ይህ ኃይል ለህልውና ትግሉ ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት መንገድ እንዲመቻች የመንግስትን በር በተደጋጋሚ ስናንኳኳ ቆይተን በዛሬው ዕለት ከተወሰኑ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረግነው ውይይት ወደ ውጊያ መግባት ስለምንችልበት እና ህዝቡን ለህልውና ዘመቻው በጋራ ስለምንቀሰቅስበት ሁኔታ መግባባት ላይ ደርሰናል።
በመሆኑም ለመላው ፋኖ አባሎቻችን፣ ለመላው የአማራ ህዝብ፣ ለልዩ ኃይል፣ መከላከያ እና ምሊሻ ተከታዩን ጥሪ እናቀርባለን:-
1/ ትጥቅ የሌላችሁ ወደፊት የምናደርገውን ጥሪ የምትጠብቁ ሆኖ መሳሪያ ያላችሁ የህዝባዊ ኃይሉ (ፋኖ) አባሎቻችን የግል ትጥቃችሁን እና የዕለት ስንቃችሁን በመያዝ ከነገ ጧት ጀምሮ ወሎ-መካነ ሰላም እንድንገናኝ ይሁን፤
2/ ይህንን ወረራ መቀልበስ አማራን እንደ ዘር የማስቀጠል-ያለማስቀጠል ጉዳይ እንጅ የፖለቲካ ጉዳይ ስላልሆነ ማንኛውም አቅሙ ያለው ግለሰብ ከአደረጃጀታችን እና ከመንግስት ጎን በመሰለፍ የከበበንን የጥፋት ናዳ በፍጥነት ለማለፍ ጥረት ያድርግ፤
3/ በዘመቻው ላይ እየተሳተፋችሁ ያላችሁ የመከላከያ፣ የልዩ ኃይል እና የምሊሻ አባላት “መሪ የለም፣ ሴራ አለ…ወዘተ” የሚሉ ምክንያቶችን ለግዜው ወደ ጎን ትታችሁ ብቻችሁን ብትቀሩ እንኳን ጠላትን ይዛችሁ ለመውደቅ ቁርጠኝነቱ እንዳይለያችሁ።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
ጥቅምት 27/2014 ዓ.ሞ
ባሕር-ዳር
የአማራ ህዝባዊ ሀይል /ፋኖ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

‹‹በትግራይ ግጭት የተካሄደው የምርመራ ሪፖርት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት አግኝቷል›› – ዶክተር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር

Next Story

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ለኢትዮጵያ ያላቸውን ድጋፍ አሳይተዋል

Go toTop