ጦቢያ እናቴ !

November 7, 2021
ጎብጣ የምትቃና በመከራ አልፋ
ወድቃ የምትነሳ ከፊት ተሰልፋ
እጇን ከቶ አትሰጥም ዛሬን ተሸንፋ
ምኞቷ ሳይሰምር ሳትቀመጥ አርፋ
የመከራው ማእበል ችግሯም ቢበዛ
ውጣ ዝም የምትል አቅልላ እንደዎዛ
ተመስገን የምታውቅ ፈጣሪውን ይዛ
የነገን ተስፋውን በሆዷ እርግዛ
ቁንጅናዎ ቢረግፍ ወዘናዎ ደርቆ
ስጋዎ ቢከሳ ከላይዎ ላይ አልቆ
ሐዘን ቢበዛባትም ነፍሷን እስጨንቆ
የእናትስ ምርቃት መሬት አይቅር ወድቆ
የመከራን ዳገት ትንፏቅቃ የወጣች
በደከመው ክንዷ ሰንደቅ ያነገበች
የእመ-እምላክን ሐገር ከአውሬ የታደገች
እቻትና ጦብያ ምስኪኗ ሐገሬ  ትውልዱን ያኮራች
እቻት እማምዬ ባለ ማሕትቧ ባለ አልባሶ-ክዳን ባለ ንቅሳቷ
እንደ አራስ ነብር አትንኩኝ የሚለው የሚቆጣው ፉቷ
ልጆቿን ሲነኩባት ክብሯን ሲያቀሉባት እይበርድም ንዴቷ
ሰንደቋን ከፍ አድርጋ ተራራው ላይ ቆማ ሐገሬን እያለች ይታያል ምሬቷ
Maraki – Sweden

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታና ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን የሚያስተላልፉት መረጃ የተለያዩ መሆናቸውን አሜሪካዊያን ጎብኝዎች ተናገሩ

Next Story

በመስቀል አደባባይ ሚሊዮኖች በአንድ ድምጽ የአሸባሪውን ሕወሓት ቡድን ግብዓተ ቀብር ለመፈጸም እንደሚገባ ገለጹ

Go toTop