- ማንኛውንም የመንግስት እና የግል ተቋም እያወደመ ነው የሸሸው
- መንገዶችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ኮሌጆችን፣ የጤና ተቋማትን፣ ዩኒቨርሲቲዎችን፣ የመብራት መስመሮች፣ የቴሌ ሰርቨሮችን፣ ባንኮችን ከመዝረፍ አልፎ አውድሞ ነው የሸሸው
- የመከላከያን እና የኤርትራን ጦር ዩኒፎርም ታጣቂዎቹን አልብሶ የትግራይን ሕዝብ መግደል፣ እናቶቹን እና እህቶቹን መድፈር፣ ንብረቶችን መዝረፍ፣ የሕዝቡን ኑሮ በማመሰቃቀል እና ለቸነፈር እንዲጋለጥ በማድረግ ነው። ይህን ሁሉ ክፋት በሕዝቡ ላይ እየፈጸመ መከላከያን እና የኤርትራን ጦር ተጠያቂ ያደርጋል። ይከሳል ይጮሀል።
ይሄን ክፍተት ለመጠቀም ጊዜ ማባከን ያልፈለጉት ቋሚ ጠላቶቻችን እነ ግብፅ ካፍ ካፉ እየተቀበሉ ክሱን ያስተጋቡለት ጀመር። የኢትዮጵያ መንግስት የምዕራባዊያንን ጫና ለመቀነስ፣ የህወሓትን ተፈጥሮአዊ ባህሪ ለማሳየት ጭምር ( የኔ ግምት ነው) ጦሩን ከትግራይ አውጥቶ የተናጠል የቶግስ አቁም አውጆ ትግራይን ለቆ ወጣ። ትህነግም ሸሽቶ ከተቀረቀረበት ዋሻ በመውጣት ከሕዝቡ ጋር ተፋጠጠ። እንደመንግስትም እንደ መሪም መቀጠል የሚችልበት አቋም ላይ ያልሆነው ጁንታ በሕዝቡ ደካማ ጎን ገባ።
ተነስ ወንድ፣ ሴት፣ ሕፃን፣ ሽማግሌ፣ ወጣት ሳትል ተንቀሳቀስ አለው። ባንክ የለ፣ ኔቶርክ የለ፣ ንግድ የለ፣ ትምርት የለ፣ ደሞዝ የለ፣ አበል የለ? መጀመሪያኑ ይህ እንዲሆን አመቻችቷል። ተነስ ይሄን ያረገህን ውረር፣ ዝረፍ፣ ብሎ ለተወራሪው ስም ሰቶ አሰለፈው። በሕዝብ ማዕበል ወረራ ጀመረ፣ አሁንም ቀጥሎበታል። አላማው አራት ኪሎ በመመለስ ሙሉ በሙሉ የሀገሪቱን የመንግስት ስልጣን መቆጣጠር ነው። ይህ ካልተሳካ ሀገሪቱን ማፍረስ ነው። ያሰለፈው ሀይል ከመውረር እና መዝረፍ፣ ባሻገር የጥላቻ ዘረኝነት ካልሆነ የሚያራምደው ርዕዮትም፣ አላማም የለውም። ከተበተነ ተበተነ ነው። ከተመታ ተመታ ነው። ስለዚህ ይህ ሀይል ወደ ማሰቢያው እንዳይመለስ በጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ልቦናውን አውሮ እንደከብት ይነዳዋል።
በህዝብ ማዕበል ተወሮ የሚዘረፈው፣ የሚገደለው የሚፈናቀለው፣ ባልበደለው? በማያውቀው የበቀል ማወራረጃ የሆነው ሕዝብ፣ እራስን የመከላከል ተፈጥሮአዊ መብቱን መጠቀም ሲጀምር ውጤቱ ትህነግ ቀምሮ ከሄደበት በተቃራኒው ይሆናል። ወረራውም ለጊዜው ጉዳትን ያስከትላል እንጂ ባጭር ጊዜ ይቀለበሳል። የጠላትህን የጭካኔ ጥግ ካየህ አንተም የግድ ላለመጥፋት ጭካኔን ከሱ ትማራለህ። አንተን ለማጥፋት በሚመዘው ሰይፍ ትሰይፈዋለህ፣ ላለመሞት መግደል ትጀምራለህ። እንተን በመውረር ሊያጠፋህ የወረረህ ጠላት፣ እሱን እንዴት ማጥፋት እንደምትችል ጭካኔውን ያስተምርሀል። እየሆነ ያለውም ይሄው ነው።
ወረራው ይቀለበሳል፣ ትህነግ ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ከምድረ ገፅ የሚያጠፋውን ጭካኔ አስተምሮናል። በሄደበት መንገድ ተጉዞ ትህነግን ማጥፋት ዋጋ ቢያስከፍልም አይቀሬ ነው።