የአማራንና የአፋርን አንዳንድ ወረዳዎችንና አንዳንድ ዞኖችን የማስለቀቅ፤ የማስለቀቅ ብቻ ሳይሆን አማራ ክልል የገባው ኃይል ሁለተኛ ወደአማራ ክልል ዝር እንዳይልና ለኢትዮጵያም ስጋት በማይሆን ደረጃ ይመታል።
ስለ አሸባሪው ህወሓት ስናስብ ከአማራ መሬት የማስወጣትን ሃሳብ አይደለም የምናስበው። ያሰመርነው መስመርም የለም። አሸባሪ ቡድኑ ለአገሪቱ ህልውና አደጋ በማይሆንበትና ለውጭ ቅጥረኞች ተገዝቶ ለኢትዮጵያ መፍረስ በማይሰራበት ሁኔታ መመታት አለበት።
በአገርም ላይ የህልውና አደጋ የደቀነው ወያኔ ነው እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ሕዝብ ላይ የደቀነው የህልውና አደጋ የለም ያሉት ጄኔራል ብርሃኑ፤ ከትግራይ ለቅቀን ስንወጣ ያደረገውን አይተናል ብለዋል።
አሸባሪ ቡድኑ በትግራይ መብራት አጥፍቶ፣ የግንኙነት መስመሩን አቋርጦ፣ ሕዝቡ ርዳታ እንዳያገኝ ከልክሎ፣ ህጻናትን አስገድዶ በጦርነት አሰልፎ ሲያስፈጅ መቆየቱን አስታውሰዋል።
(ኢ ፕ ድ)