‹‹ሸኔ አሸባሪው ህወሓትን ወደ ስልጣን የመመለስ እንጂ ወደ ጫካ የሚወስድ የኦሮሞ ጥያቄ የለውም››

September 29, 2021
– አቶ ታዬ ደንደአ የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ታዬ ደንድአ
ታዬ ደንድአ

የሸኔ ጥረት አሸባሪው ህወሓትን ወደ ስልጣን የመመለስ እንጂ የትጥቅ ትግል ለማድረግ ወደ ጫካ የሚወስድ የኦሮሞ ጥያቄ የለውም ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደአ ገለጹ፡፡

አቶ ታዬ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የሸኔ ጥረት አሸባሪው ህወሓትን ወደ ስልጣን የመመለስ እንጂ የትጥቅ ትግል ለማድረግ ወደ ጫካ የሚወስድ የኦሮሞ ጥያቄ የለውም፡፡

የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎቹ ብሄር ብሄረሰቦች ጋር በመቀናጀት ባደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል በዴሞክራሲ ጭምብል ፍጹም አምባገነን ሆኖ የዴሞክራሲን ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ሲጨፈጭፍ፣ ሀብት ሲዘርፍና ሲያዘርፍ የኖረው የአሸባሪው ህወሓት መራሹን መንግስት አሽቀንጥሮ ጥሏል፡፡

የኦሮሞ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ የነበሩት የእኩልነትና የአንድነት ጥያቄ መልስ አግኝተው ማጣጣም ጀምረዋል ብለዋል።

‹‹ሸኔ ግን ለአንድነትና ለእልኩልነት አልገዛም፡፡ በማለት ወደ በረሃ የገባው አሸባሪው ትህነግ ለመታደግ በድሉ ማግስት ወደ ጫካ መግባቱ ሸኔ በህወሓት ሳንባ የሚተነፍስና በህወሓት አዕምሮ የሚያስብ ቡድን መሆኑን ያሳየ ክስተት ነው›› ብለዋል፡፡

የደቡብ ኦሮሚያ የሸኔ ታጣቂ አዛዥ አቶ ጎልቻ ዴንጌ የቡድኑን እኩይ ድርጊት በመቃወም ወደ ሰላማዊ ትግል መመለሱ በይበልጥ የቡድኑን ማንነት እርቃኑን ያስቀረ ውሳኔ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

(ኢ ፕ ድ )

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የቀረቡትን የምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ እና ምክትል ከንቲባ ሹመቶችን አፀደቀ

index
Next Story

የ100 ቢልየን ብር ሃብት የ100+ ሚልየን ህዝብ ጉዳይ ነው፤ – ነብዩ ስሁል

Go toTop