ጀነራል አበባው ታደሰ በወሎ ግንባር በሰሜን ወሎ ግምባር

September 19, 2021
242124190 10160397822374587 7262219884801159733 nየኢፌዴሪ መከላከያ ምክትል ጠ/ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ በሰሜን ወሎ ግምባር ተገኝተው ከዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በግዳጅ አፈፃፀም ዙሪያ ተወያዩ።
በግምባሩ የተገኙት ም/ጠ/ኢታማዦር ሹሙ ፣ ለምንም የማይበገረው ሠራዊታችን ከቀደምት የኢትዮጵያ ታሪክ በመነሳት ለህይወቱ ሳይሳሳ በሀገሪቱ ህልውና ላይ የተጋረጠውን አሸባሪ ሀይል ለመደምሰስ እያደረገ ያለውን ስኬታማ ኦፕሬሽን አድንቀዋል።
ጀነራል አበባው ፣ ሠራዊታችን በተደጋጋሚ የሚያስመዘግባቸው ድሎች የሽብርተኛውን ሀይል ለመደምሰስ አስተማማኝ ቁመና ላይ በመሆኑ ለላቀ ግዳጅ አፈፃፀምም የወትሮ ዝግጁነት አቅም የመፍጠሩ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ በበኩላቸው ፣ ሰራዊታችን ህዝባዊነት ባህሪውን አስጠብቆ አሸባሪውን ሀይል አንገት እያስደፋ የወረራቸውን አንዳንድ ቦታዎች በማስለቀቅ አኩሪ ታሪክ እየሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል ፡፡

242212720 10160397822619587 979849300073702105 n

አሸባሪው የትህነግ ቡድን በህዝብ ላይ እያሳደረ ያለውን ግፍና በደል በመገንዘብ በአጭር ጊዜ እርምጃ በመውሰድ የተፈናቀለውን ማህበረሰባችን ወደ ቀየው እንዲመለስ ለማድረግ ግምባር ላይ ያለው ሀይላችን የጠላትን ቅስም እየሠበረ ነው ብለዋል።
ተቋሙም በአሁኑ ሠዓት ብቁ ሠራዊትን በማፍራት አስተማማኝ የዝግጁነት ምዕራፍ ማጠናቀቁንም ተናግረዋል።(ኢፌድሪ መከላከያ)
(ኢፌድሪ መከላከያ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

242321284 3028674050708387 5462023528350303105 n
Previous Story

አሜሪካን ጨምሮ አንዳንድ አጋር ሀገራት ያስመዘገብናቸውን ከፍተኛ ድሎች ለመመስከር አለመድፈራቸው እንቆቅልሽ ነው- ሙፈሪያት ካሚል

Next Story

የሁለት ደብዳቤዎች ወግ ከአዲስ አበባ እና ከመቀሌ – መሳይ መኮነን

Go toTop