ዩኤንኤችሲአር ከትግራይ ክልል ወጥተው በሱዳን መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ስደተኞች ቁጥር መቀነሱንና ስደተኞቹ የት እንዳሉ እንደማያውቅ ገለጸ

September 8, 2021
mikeidra k
mikeidra k
ጷጉሜ 03 ቀን 2013 (ኢዜአ) የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) ከትግራይ ክልል ወጥተው በሱዳን መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በጦርነት ይሳተፉ ወይም የት ይሂዱ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ገለጸ።
ዩኤንኤችሲአር ባወጣው መግለጫ ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው በሱዳን መጠለያ ጣቢያ የሚገኙና ድጋፍ የሚደረግላቸውን ስደተኞች የመረጃ ሁኔታን ከልሷል።
በዚሁ መሰረት በመጠለያ ጣቢያው ተመዝግበው የነበሩ ስደተኞች ቁጥር ከቅርብ ወራት ወዲህ መቀነሱንና በስደተኛነት ተመዝግበው የነበሩ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ይመለሱ ወይም የት ይሂዱ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ይፋ አድርጓል።
በግጭት ውስጥ የተሳተፈን ሰው በስደተኛነት የማይቀበለው ዩኤንኤችሲአር በስደተኛነት ተመዝግቦ በግጭት ውስጥ የተሳተፈ ማንኛውንም ሰው ዳግም እንደማይቀበል ይፋ አድርጓል።
ከኢትዮጵያ ግጭት ሸሽተው በሱዳን መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ተጠልለዋል የተባሉት ስደተኞች አብዛኛዎቹ ወጣቶች መሆናቸው ብዙውን ጊዜ በግጭት ምክንያት ለስደት ከሚዳረጉ ህጻናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች ተቃራኒ መሆኑ አነጋጋሪ እንደነበር ይታወቃል።
ወጣቶቹ በአሸባሪው ህወሃት የሰለጠኑ ታጣቂ ወጣቶች እንደሆኑና በማይካድራ ጭፍጨፋ የተሳተፉ ‘ሳምረ’ በሚል ስያሜ የሚታወቁ እንደነበሩ በተደጋጋሚ ተገልጿል።
እነዚህ ወጣቶች አሸባሪውን ቡድን የሚያደርገውን የሽብር ድርጊት ተቀላቅለው ለማገዝ ድንበር አቋርጠው ለመግባት ተደጋጋሚ ሙከራ አድርገው ሙከራቸው እንደከሸፈ ይታወሳል።

Ethiopian News Agency

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት የ2014 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት ለመላው ምዕምናን ያስተላለፉት መልዕክት

ooo
Next Story

የቢራ ፋብሪካ “ጁንታ” መኖሩን ስንቶቻችን እናውቃለን? – ግርማ በላይ

Go toTop