የጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ዛሬ ከሰዓት በጠሩት የጂ-20 ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ የተሰኘ ጉባዔ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበይነ መረብ በመታገዝ ተሳትፈዋል።
“ለንግድ እና ለኢንቨስትመንት ማዕቀፋዊ ሁኔታዎች” በሚል ርዕስ የሚካሄደው ጉባዔ የስምምነቱ ፈራሚ የሆኑ ሀገራት ተጨማሪ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እንዲያገኙ በሚያስችል ሁኔታ ማዕቀፋዊ ሁኔታዎችን ወደ ቀጣይ ርምጃዎች ለመውሰድ የታለመ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር፣ ለሙዐለ ነዋይ ፍሰት ምቹ ነባራዊ ሁኔታ እንዲኖር ለማስቻል በኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አማካኝነት ማክሮ ኢኮኖሚያ፣ መዋቅር እና የዘርፍ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን እንደገለጹ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
(ኢ.ፕ.ድ)