“ጠላት አለኝ ከሚለው የደጀን ኃይሉ እየራቀ በመጣ ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ወጥመዱ እየገባ ነው”፦ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ

August 5, 2021

gizachew

ጠላት አለኝ ከሚለው የደጀን ኃይሉ እየራቀ በመጣ ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ወጥመዱ እየገባ መሆኑን የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አስታወቀ

ፓርቲው ወቅታዊ አገራዊ ጉዳይን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል፦

ድል ያለመስዋዕትነት የማይታሰብ ነው!
ታሪካዊ ከተሞቻችንም ሆነ አጠቃላይ የአማራን ግዛት ከጠላት ወረራ መመከት የሚቻለው በጠንካራ አደረጃጀት፣ በወታደራዊ ዲሲፕሊን እና በትግል ዓላማ ጽናት በመታገል ነው፡፡
ጠላት በየአቅጣጫው የሚነዛቸው የሽብርና ፈጠራ ወሬዎች በትግላችን ላይ ተጽዕኖ እንዲኖራቸው መፍቀድ የለብንም፡፡
ጠላት አለኝ ከሚለው የደጀን ኃይሉ እየራቀ በመጣ ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደወጥመዱ እየገባ ነው፡፡ ያለምህረት የምንቀጣውም በዚህ አግባብ ነው፡፡ እየሆነ ያለውም ይኼው ነው፡፡ ይሁን እና ምንጫቸው ባልታወቁ የጠላት ወሬዎች ከመደናገር ራሳችን መቆጠብ ይኖርብናል፡፡
ምንግዜም ቢሆን የመረጃ ምንጮቻችን በሙሉ የኃላፊነት ስሜት የሚንቀሳቀሱት የሕዝባችን ሚዲያዎች እና በየደረጃው ያለው አመራር እንጅ ሌላዉ ኃይል ሊሆን አይገባም፡፡
ያለነው የህልውና ትግል ላይ ነው፡፡ በግንባር የሚገኘው የወገን ጦር ፊት ለፊት ጠላትን እየሰበረ ይገኛል፡፡ ወደወጥመዱ እያሳበ ወደመቃብር ማውረዱን ይቀጥላል፡፡ የምስራቅ አማራ ሰሜን ወሎ ተራሮች የወራሪው ትህነግ መንጋ መቀበሪያ ይሆናሉ፡፡ አርሶ አደራችን ጎተራውን ሊያራቁት፣ ሚስቱን ሊደፍር፣ ልጁን ሊያፍን፣ ወጣቶቹን ሊገድል፣… የመጣውን መንጋ በቆራጥነት ስሜት እየተፋለመው ነው፡፡
በየጫካውና ሰርጡ እየተሳደደ ያለው አሸባሪ ከአማራ መሬት በድን ሬሳው እንጂ ከእነ እስትንፋሱ እንዲወጣ አንፈቅድለትም፡፡ ከውጊያ ግንባሮች ርቃችሁ የምትገኙ ውድ የአማራ ልጆች፣ የክልላችን ሕዝብና መላ ኢትዮጵያዊያን በጠላት ትህነግ የሚነዛውን ሐሰተኛ ወሬ ቦታ ባለመስጠት የሥነ-ልቦና ጦርነቱ በበላይነት መምራት ይኖርብናል፡፡
በእርግጠኝነት የምንናገረው ነገር ጠላት ጨርሶ ወደ መቃብር መውረዱ አይቀሬ ስለመሆኑ ነው፡፡ የሰው ልጅ ቀርቶ እንስሳት እንኳ በጦርነት ሕይወታቸው እንዲያልፍ የማንሻ ቢሆንም ወራሪን መቅጣት ጥንትም የአባቶቻችን ነውና ሞት ምርጫው ለሆነ ጠላት ምህረት የለንም፡፡ በማዕበል የሚዝል ክንድ እንደሌለን የሰሜን ወሎ ተራሮች ዘላለማዊ የታሪክ ምስክር እናደርጋቸዋለን!
ከደጀኑ የሚርቅ ግን ደግሞ ለሞት የተሰለፈ ጠላት ወደ መቃብር መውረዱ ይቀጥላል፡፡ ይህ ድል ያለመስዋዕትነት የማይታሰብ ነው፡፡
ቁምነገሩ ትርጉም በሚሰጥ መስዋዕትነታችን ታሪካዊ ከተሞቻችን ብቻ ሳይሆን የአማራ ሕዝብ እና የኢትዮጵያ ህልውና መጽናት መቻሉ ነው፡፡
መሰልጠን፣ መደገፍ፣ መዝመት የህልውና ትግላችን የማይገሰሱ መርሆዎች ናቸው፡፡
ድል ያለመስዋትነት አይታሰብም!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

image 2021 08 05 132504
Previous Story

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት መግለጫ

227853252 4254020138016412 6248644924618750209 n
Next Story

ህዝብ መሳሪያ ባይኖረው እንኳን ድንጋይን መሳሪያ፣ አንድነትን ጥይት ማድረግ ይችላልል!

Go toTop