Español

The title is "Le Bon Usage".

እነርሱም እኛን ፤እኛም እነርሱን እንላለን ! – ማላጂ

በአገራችን ለረጅም ዓመታት በህዘብ ሠላም መደፍረስ እና የአገር አንድነት ላይ ከፍተኛ ሴራ በራሱ አገሪቷን ሲመራ በነበረ የልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ይከናወን እንደነበር ዓለም የሚያዉቀዉ ፀሀይ የሞቀዉ  የአደባባይ ጉዳይ ነዉ ፡፡

ለዚህም ዋነኛ ምክነያት ለህዝብ እና አገር የነበረ ጥላቻ እና ንቀት መሆኑን ለአለፉት የረጅም ዓመታት የመከራ ዘመን የደረሰበትን በደል እና መገለል ሊናገር የሚችለዉ ጊዜዉን ጠብቆ በሚሰራ ታሪክ እና የደረሰበት ህዝብ ብቻ ነዉ ፡፡

ከሶስት ዓመት በፊት በህዝብ ያላሳለሰ ትግል እና ህዝባዊ አገር ወዳድ ኢትዮጵያን በከፈሉት ዘርፈ ብዙ  መስዋዕትነት አንጻራዊ እፎይታ ቢገኝም በህዝብ እና አገር ላይ ሲደረግ የነበረዉ ክህደት እና ዕልቂት በዓይነት እና መጠን እየጨመረ በመምጣቱ ቀድሞ ለዓመታት የህዝብን ስልጣን ለግል እና ለቡድን ጥቅም ሲገለገሉበት የነበሩት ብሄራዊ ኃላፊነታቸዉን ወደ ጎን ትተዉ በህዘብ ላይ ባደረሱት የኣመታት ኢሰባዊ እና ኢ-ተፈጥሯዊ  ግፍ እንዲሁም የአገሪቷን ሉዓላዊነት እና ዳር ድንበር ከማስደፈር ባለፈ ተጠያቂ ባለመሆናቸዉ ዛሬም በዚያዉ መንገድ ቀጥለዉበታል ፡፡

ይህም ቢዘገይም በአገር ክህደት እና ሽብር እንዲፈረጁ መንግስት ድንጋጌ በማዉጣት በህግ  አሸባሪ በሚል “ትህነግን /ህወኀትን  ” እና ግብረ አበሮችን ተጠያቂ አድርጓል፡፡

ነገር ግን የዚህ ኃይል  የገንዘብ ምንጭ  መንግስት ከመሆኑ አስቀድሞ፣ መነግስት ሆኖ እና መጋቢት 24/210 ዓ.ም. ከስልጣን ማማዉ ከተገፋ በኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ (የአገሪቷ) አንጡራ ሀብት እና ንብረት እንደነበር እና እንደሆነ በግላጭ የሚታወቅ ነዉ ፡፡

ይኸዉም በከተሞች ያሉትን በህዝብ እና መንግስት ተቋማት ስም በግል እና በቡድን ከሚዘወሩት ሌላ በደም ዋጋ/ከሳ  (Endowment fund ) ፣ በ ኤፍርት ፣ በተለያዩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ስም እና ጥላ ስር ያልወደቀ የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ሀብት ንብረት እንዳልነበር በግልፅ የሚታወቅ ነዉ ፡፡

እናም መንግስት የሽብር አገልግሎት የሚዉል የገንዘብ ምንጭ አፋልጉኝ ሲል በህወሃት /ኢህዴግ መዳፍ ያልወደቀ የህዝብ ሀብት ቀርቶ የግለሰብ ማንነት እና ህይዎት ተገብሯል እና እንዴት የአገር ሀብት እና ንብረት የብክነት እና ጥፋት መንገድ ለማወቅ እንዴት ዛሬ ላይ ሆኖ ተሳነዉ ፡፡

አዚህ ጋ በጭሩ ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ ለ27 ዓመታት ለመንግስታዊ የተቀናጀ ብሄራዊ ምዝበራ መንገድ የተቀየሰዉ የመንግስት/ የህዝብ ኃብት ወደ ግል ማዞር (privatization procedure /Investment) በሚል በጦርነት በተጎዱ አካባቢዎች ወዘተ ዓይነተኛ እና ብቸኛ የዘረፋ ዕቅድ ነበር ፡፡

ለዚህም በአራት ዋና ዋና ዋና የልማት እና ማስፋፋት ጥላዎች ማለትም ፡-

  • ኤፈርት፣
  • በየአካባቢዉ በክልል እና ህዝብ ስም የተከፈቱ የልማት ተቋማት(አምባሰል ፣ዲንሾ፣ ጉና…….)፣
  • ሚድሮክ ፣
  • የስርዓቱ ቅርብ እና ታማኝ አገልጋይ የነበሩ ግለሰቦች ፣ቡድኖች እና ማህበራት የሚገኙበት ነዉ ፡፡

እዚህ ጋ በስም የተጠቀሱት ሁሉ በሽፋንነት  እንጅ በስማቸዉ የሚጠራ የነበረዉ ሁሉ የነርሱ እንዳልነበር ነገር ግን በእነርሱ ጥላ ስር በአገር እና ህዝብ ላይ በደል እየደረሰ መሆኑን ያላወቁ ይኖራሉ ባይባልም በአቋቋሙት ድርጅት ስም ኢሰባዊ እና ብሄራዊ አሻጥር ሲሰራ አለማወቃቸዉ ወይም አለማስተካከላቸዉ ጊዜዉ ሲደርስ በህዝብ እና ታሪክ ተጠቃሸ እና ተወቃሽ መሆናቸዉ አይቀርም፡፡

ይህንም በዝርዝር ለማሳየት ኤፈርት  ለአብነት ከኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት በተለያየ መንገድ( ምርኮ፣ ዝርፊያ፣ቅሚያ…..) ያገኘዉን  ሀብት እና ንብረት የግል እና የቡድን ሀብት ማድሩ፣

የአዲግራት መፍሃኒት ማምረቻ የግለሰብ ሀብት እና ጉልበት ያለበት እና የተቀማ…..መሆኑ ሲታወቅ፣

በሚድሮክ ስም  በሚጠሩ ነገር ግን የሜድሮክ ስለመሆናቸዉ አንድም ቀን የድርጅቱ ባለቤት ያረጋገጡበት ወይም ያስተባበሉበት ማስረጃ በሌለበት በሜድሮክ ጥላ ስር የሚገኙ ትላልቅ ሰፋፊ የኢትዮጵያ እና ህዝቧ የልማት ድርጅቶች ፡-

ደቡብ ፡

  • በበቃ ቡና ተክል ፣
  • ቴፒ ቡና ተክል ፣
  • ወሽ ዉሽ ሻይ ልማት ፣
  • ጎጀብ እርሻ፣
  • በኢልባቦር ፡ ጉማሮ ቡና ተክል
  • በጎጃም ብር ሸለቆ ( ላይ ብር ፣ ታች ብር ፣አየሁ)፣

በእነዚህ ተቋማት በተለይም ከ 1997 ዓ.ም ጀምሮ አስከ 2010 ዓ.ም ድረስ በበላይነት ሲያዝዝባቸዉ እንደነበር  ለሚያዉቅ እነዚህ በስም እንጅ  የሚድሮክ አጋር ተቋማት ናቸዉ ለማለት አይቻልም ፡፡

ሚድሮክ ሲጀምር ዓላማዉ አገር ለማሳደግ ፣ ስራ አጥነት ለመመከት ብሎም የአገሪታን የመልማት ፍላጎት እና ዕምቅ ዕድል በመጠቀም ከራስ አልፎ ለጎረቢት መሆን ወደ መቻል እንደነበር በጊዜዉ የምናወቀዉ እና የተነገረ ዕዉነታ ነዉ ፡፡

ሆኖም ከዚህ በተቃራኒ ለ20 ዓመት እና ከዚያ በላይ ያገለገሉ ሠራተኞች ያለምንም ጡረታ ፣ ዳረጎት እና የስንብት ክፍያ እንደ ዛገ ቆርቆሮ ከነቤተሰባቸዉ ተብተነዋል ፡፡ ይህን ሚድሮክ ወይም የሚድሮክ ስራ ነዉ ለማለት የሚቻል አይደለም ፡፡

ነገር ግን በተለይ ከ2002 ዓ.ም ምርጫ በኋላ በሚድሮክ ስም እና ጥላ ስር ለተወሸቁ የህዝብ ተቋማት የመንግስት አይሏቸዉ የግል  በህወሀት በቀጥታ እና በሰዉር  ይመሩ  እንደነበር  የአደባባይ ሀቅ ነዉ ፡፡

ለዓመታት በ600 ብር የወር ደምዎዝ ሲማቅቅ የነበር ወዛደር እየተፈናቀለ  ባለሶስትዮሽ  ደምዎዝ ተከፋይ ታጋይ(ከዝቅተኛ አስከ ከፍተኛ ማእረግ ጡረተኛወታደር) በሚጠይቀዉ እና በፈለገዉ ልክ እንዲመደብ እና እንዲከፈለዉ ይደረግ ነበር ፡፡ ይህም ሌላዉ ባለሙያም ሆነ ነባር ሠራተኛ ልማት ድርጅቶችን  ከማቋቋም አስከ ማስፋፋት ያደረሰ ለድርጅቶች ደህነት ስለማይታመን እንደነበር የሚረሳ አይደለም ፡፡

በግለሰብ ስም የተያዙ የዘመናት ነባር የህዝብ የልማት ተቋማትም ሆኑ አደዲሶች( ጋምቤላ፣ ደቡብ፣ መተከል፣በሸዋ ሰፋፊ የፍራፍሬ እርሻዎች …..) የነማን እንደነበሩ ከታወቀ ዛሬ አገሪቷን እና ህዝቧን ቁም ስቅል የሚያሳየዉ ህወሃት እና ተባባሪዎች የጉልበት ሰጪ ምንጭ የህዝብ እና የመንግስት ሀብት  ስለመሆኑ አይጠራጠርም ፡፡

ሳር ቅጠሉን የሚዝዙበት እንደነበር አስከታወቀ ድረስ ከምንጩ የህዝብ እና የመንግስት ተቋማት ለአገር ልማት እና ዕድገት ለማዋል የተቋማት ገቢ እና ወጪ ቦይ / ፈር በጥብቅ መከታተል እና ማስተካከል ይጠይቃል ፡፡

ለዚህም አንጀት ካለ ዕንባ አይገድም እንዲሉ አበዉ የምዝበራ በሮችን እና ቦዮችን ለመዝጋት መንግስት እና ህዝብ በቁርጠኝነት እና በህብረት ከቆሙ “አሸባሪ እና አስሸባሪ”  ከባህር የወጣ አሳ ማድረግ አያዳግትም  ፡፡

ከዚህ ዉጭ ዛሬም እንዳለፈዉ በተለምዶ ጩኸቴን ቀሙኝ ንግግራቸዉ  ህዝብን እና አገርን የሚያሸብር ፤የሚዘብር መንግስት ነዉ በማለት …..የቆየዉን የአገራችንን የቡዶች መንደር ጠያቂ ሠዉ እና የተጠያቂ መልስ …“እነርሱም እኛን ይላሉ እኛም እነርሱን እንላለን   ”እናዳይሆን  ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ !!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የኢትዮ ቴሌኮም ለውጪ ሀገር ድርጅት ይሸጥ ወይስ አይሸጥ ? (መላኩ ከአትላንታ)

2021 06 13 15.10.15
Next Story

ሀገራችንን በማስቀደም ምዕራባዊያነ እናሸንፍ (በጋዜጠኛ ቶማስ ሰብስቤ)

Zehabesha | Ethiopian Latest News, Top Analysis & Best Articles <h1 style="text-align:center">tHE HABESHA Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win</h1><title> <title><h2 style="text-align:left">Get the Best Scholarly Articles and Analysis on ZeHabesha</h2><title> <title><h3 style="text-align:right">Zehabesha Ethiopian News</h3><title> <title><h4 style="text-align:justify">Ethiopian Lates News</h4><title> <meta name="keywords" content="Ethiopian News, Ethiopia News, Ethiopian News Today, Top Stories, The Habesha, Latest News, Ethiopia, Breaking News, zehabesha, zehabesha Amharic News, The Habesha News, Headlines, borkena. bbc amharic, repoter, mereja, Ethiopian News provider"> <!-- Google Tag Manager --> <script>(function(w,d,s,l,i){w[l]=w[l]||[];w[l].push({'gtm.start': new Date().getTime(),event:'gtm.js'});var f=d.getElementsByTagName(s)[0], j=d.createElement(s),dl=l!='dataLayer'?'&l='+l:'';j.async=true;j.src= 'https://www.googletagmanager.com/gtm.js?id='+i+dl;f.parentNode.insertBefore(j,f); })(window,document,'script','dataLayer','GTM-5WDL6STX');</script> <!-- End Google Tag Manager --> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=G-W9E3TWE2TL"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'G-W9E3TWE2TL'); </script> <meta name="msvalidate.01" content="4781C31A916C7AB883D8AF1F4F3BFC49" /> <link rel="icon" href="/path/to/favicon.ico"> <link rel="icon" type="image/png" href="/thehabesha.com/favicon-96x96.png" sizes="96x96" /> <link rel="icon" type="image/svg+xml" href="/thehabesha.com/favicon.svg" /> <link rel="shortcut icon" href="/thehabesha.com/favicon.ico" /> <link rel="apple-touch-icon" sizes="180x180" href="/thehabesha.com/apple-touch-icon.png" /> <link rel="manifest" href="/thehabesha.com/site.webmanifest" /> <meta name="seobility" content="48b995a16caf3ab9d546a000c18b65d3"> <main> <!-- Main content of your page goes here --> </main> <script type="text/javascript" src="//cdn.rlets.com/capture_configs/d2b/aac/e54/1fc4f7ea32cf1e1d818a0f2.js" async="async"></script> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=TAG_ID"></script> <script src="https://www.googleoptimize.com/optimize.js?id=OPT-M8Z33GL"></script> <meta name="google-site-verification" content="Lf_65x5pXGn-W1TA8CsfJi-53aAyIKdfVyM_QkwpvgY" /> <head> <title>Ethiopian Latest News: Top Analysis and the best Articles<title> <script defer data-domain="thehabesha.com/mEUHSv" src="https://api.publytics.net/js/script.manual.min.js"></script> <script> window.publytics = window.publytics || function() { (window.publytics.q = window.publytics.q || []).push(arguments) }; publytics('pageview'); </script> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=UA-215686007-9"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'UA-215686007-9'); </script> <script async src="https://pagead2.googlesyndication.com/pagead/js/adsbygoogle.js?client=ca-pub-9091845805741569" crossorigin="anonymous"></script> <script async custom-element="amp-ad" src="https://cdn.ampproject.org/v0/amp-ad-0.1.js"></script> <title>Zehabesha Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win