ቅን ልቦና ካለ (ዘ-ጌርሣም)

October 8, 2020

ቅን ልቦና ካለ የሚያቅት አይኖርም
እያንዳንዱ ዜጋ ከጣረ ለሰላም

ተፈጥሮ ያልዳኘው
ወሰን ያልገደበው
ሚዛን ያልጠበቀ
መስመር የለቀቀ
ውሃ ሞልቶ ሲፈስ
እየጠራረገ ሁሉን በማግበስበስ
ይገባል ወደ ወንዝ
ፍሰቱን ለማገዝ
ከዚያ በኋላማ ሃይሉን አጠናክሮ
ፏፏቴ በመሥራት ሽቅብ ተፈናጥሮ
ይተፋል ሞገዱን
በማርጠብ ዙሪያውን

ቅን ልቦና ካለ የሚያቅት አይኖርም
እያንዳንዱ ዜጋ ከጣረ ለሰላም

የሞገዱን ግፊት
ጥቅሙን ያልተረዱት
ሰጥመው ይቀራሉ
ወይ ይጠረጋሉ
እንደ ደረቀ ዛፍ
የሌለው ቅርንጫፍ

ቅን ልቦና ካለ የሚያቅት አይኖርም
እያንዳንዱ ዜጋ ከጣረ ለሰላም

ዘዴውን ያወቁት
በዕውቀት የመጠቁት
ኃይል በማመንጨት
አገርን በማልማት
ወጥተው ከድህነት
ከተመፅዋችነት
ስደትን አስቁመው
ዜጎችን አጥግበው
ሁሉም በሀገራቸው
ይኖራሉ ኮርተው

ቅን ልቦና ካለ የሚያቅት አይኖርም
እያንዳንዱ ዜጋ ከጣረ ለሰላም

በግልፅ ውይይት
አጥፍተው ልዩነት
ተጋግዘው በጋራ ይበለፅጋሉ
ጤናማ ቤተሰብ ይመሰርታሉ
ታሪክ ተረካቢ ትውልድ ያፈራሉ
ሁሉም ጠግቦ አዳሪ ሆነው ይኖራሉ

ቅን ልቦና ካለ የሚያቅት አይኖርም
እያንዳንዱ ዜጋ ከጣረ ለሰላም

በትምህርት መበልፀግ
በሀብት መበልፀግ
በሰላም መታደግ
በጤናም መታደግ
ቀና አዕምሮ ካለ
ከሚያዝን ልብ ጋር የተደላደለ
ከራስ ጋር መታረቅ
ሃሳብ ሳይሄድ ዕሩቅ
ተጠየቅ እራስን
ተጠየቅ ምላስን
ብሎ በመሞገት
ይገኛል ትርጉሙ የሰላም ምንነት
በሰላም አውለኝ
ለጎርቤቶቸም ሰላሙን ስጥልኝ
ብሎ ለተነሳ ወደ ሥራ ሊሄድ
በጭራሽ አይኖርም የማይሰልጥ መንገድ

ቅን ልቦና ካለ የሚያቅት አይኖርም
እያንዳንዱ ዜጋ ከጣረ ለሰላም

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

“ የፍፃሜው ጦርነት ነው…” መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

Next Story

“ፍቅሬ ፍቅሬ በዛ እኔ አላማረኝም” – የሀጫሉና የመታሰቢያውና ስጦታው ጋጋታ – አምባቸው ደጀኔ

Go toTop