ከሚገድለኝ ሰይጣን ይልቅ የሚሰድበኝ ባለስልጣን ይሻለኛል! – ስዩም ተሾመ

August 9, 2020

አቶ  ሽመልስ_አብዲሳ “በትላንትናው እለት የተናገረው ነው” ተብሎ የተሰራጨው መረጃ #ከሰባት_ወር በፊት #የብልፅግና_ፓርቲ ገና በምስረታ ሂደት ላይ እያለ የተናገረው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። በወቅቱ የድርጅቱን አባላትና አመራሮች በኦቦ ለማ መገርሳ፣ ወ/ሮ ጠይባ እና በዶ/ር ሚልኬሳ ከሚመራው ብሔርተኛ ቡድን ለመነጠልና በድርጅቱ ውስጥ ተፈጥሮ በነበረው የሃይል ሹኩቻ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት በሚደረግ ጥረት የተናገረው እንደሆነ ተረጋግጧል።
አቶ ሽመልስ የተናገረበት ግዜና ቦታ ምን ያህል የተለያየ ቢሆንም አዲስ አበባን አስመልክቶ የተናገረው ነገር መቼም፥ እንዴትም ትክክል አይሆንም። ይሁን እንጂ በወቅቱ ድርጅቱ ውስጥ የጃዋር መሃመድ ጉዳይ አስፈፃሚ የነበሩት ከላይ የተጠቀሱት የኦዴፓ አመራሮች ከኮዬ ፈቼ ኮኖደሚኒዬም ጋር በተያያዘ ሲያራምዱት የነበረው አቋምና ጉዳዩ በብሔርተኞቹ ዘንድ የነበረው ድጋፍ ሲታሰብ እነ ሽመልስ የነበሩትን አጣብቂኝ በግልጽ ያሳያል። ያ ባይሆን ኖሮ ተቀናቃኙ ቡድን አሸናፊ ቢሆን ኖሮ አሁን ላይ ጃዋር መሃመድ መገኛው እስር ቤት ሳይሆን ቤተመንግሥት ይሆን ነበር። ስለዚህ አቶ ሽመልስ የተናገረውን ነገር ከዚህ አንፃር ማየት ተገቢ ነው።
ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ከሰባት ወር በፊት የተደረገውን ንግግር ልክ ትላንት እንደተደረገ ተደርጎ የወጣው የጃዋር ጉዳይ አስፈፃሚዎች ለግምገማ ሲቀርቡ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። ስለዚህ የመንግስት ስልጣንና ሃላፊነት ይዘው በአክቲቪስት የሚመሩ፤ ለምሳሌ ጥቅምት 12/2012 ማታ አቶ ጃዋር መሃመድ ባስነሳው ሁከትና ብጥብጥ በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃትና ጉዳት እንዳይደርስ ከመከላከል ይልቅ የጃዋር ጠባቂ ለመሆን በውድቅት ሌሊት መኖሪያ ቤቱ ድረስ የሄዱት ለማና ጠይባ፣ ልክ በድርጅቱ ግምገማ ሲደረግባቸው ከሰባት ወር በፊት የተቀዳን ንግግር #ለፅንፈኛ_የአማራ አክቲቪስቶች Leak አደረጉ። ህዝቤ እየተነሳ እሪሪሪሪ አለ።
ነገር ግን ይሄን መረጃ አሾልኮ ያወጣው ቡድን ቀንደኛ የጃዋር ጉዳይ አስፈፃሚዎች፣ ይህንንም ያደረጉት ጃዋርንና ግብረ-አበሮቹን ለማስፈታትና እንደ ለመደው እናታችን ላይ እንዲፈነጭ ለማድረግ ነው። ስለዚህ ይህን ሴራና ተንኮል የጠነሰሱት በግምገማ ከአባልነት ሊሰረዙ እንደሆነ ሲያውቁ ነው። ነገር ግን የእነሱ ቡድን አሸናፊ ሆኖ ቢወጣ ኖሮ ሽመልስ የተናገረውን እነሱ በተግባር የሚያደርጉትን እና ያደረጉትን ነው። የኮዬ ፍቼ ኮንደሚኒየም ለነዋሪዎች ሊተላለፍ በኦሮሚያና አዲስ አበባ መካከል ያለው የድንበር ጉዳይ መፍትሔ ስላላገኘ ብለው የፃፉት ደብዳቤ ለዚህ ማሳያ ነው። በአጠቃላይ አቶ ሽመልስ ከሰባት ወር በፊት የተናገረው ከዚህ ፅንፈኛ ቡድን ጋር በነበረው የሃይል ሽኩቻ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት ነው።
“ዋሽቱ ማስታረቅ” እንደሚባለው አቶ ሽመልስ የተናገረውን ተናግሮ ድርጅቱና የክልሉ መንግስትን ከእንዲህ ያለ ፅንፈኛ ቡድን መታደግ በመቻሉ ሊያስመሰግነው ይገባል። ከሰባት ወር በፊት ሆነ ትላንት በተለይ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የተንፀባረቀውን አቋም  ፋሽታዊ ነው በማለት አውግዤያለሁ። ነገር ግን ሽመልስ ሆነ ሌላ ሰው ይሄን የተናገረው በእውን የተረጋገጠ ፋሽታዊ አቋምና አመለካከት ያላቸው አመራሮች በክልሉም ሆነ በሀገር ደረጃ አሸናፊ ሆነው እንዳይወጡ ለማድረግ በሚል ስለሆነ “እሰይ… አበጀህ” ብዬዋለሁ።
ምክንያቱም ያ ቡድን ባይገታ ኖሮ ምን ሊከሰት እንደሚችል በዚህ አመት ጥቅምት 12 እና ሰኔ 22 በተግባር አይተንዋል።
ሽመልስ የተናገረው በወቅቱ ትክክል ነው
ስዩም ተሾመ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የአርባ ቀን መታሰቢያ ለአርሲና ባሌ ሰማእታት

Next Story

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የዓይጠመጐጥ ማምረቻ!

Go toTop