ግድቡ ውኃ መያዝ ጀምሯል … ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ውኃ መያዝ መጀመሩን የሚያሳዩ የሳተላይት ምስሎች ወጥተዋል

July 9, 2020

ስለ ሳተላይት ምስሎቹ ይዘት የተጠየቁት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የቀረበላቸውን ጭብጥ አላስተባበሉም፤ እንዲያውም “እንደዚያ መውሰድ ይቻላል” ብለዋል። በምስሎቹ ላይ ትንታኔ መስጠት ግን አስፈላጊ ነው ባለው እንደማያስቡ አክለው ገልፀዋል።

በአፍሪካ ኅብረት አስተባባሪነትና ታዛቢነት “ቀሪ” በተባሉ የቴክኒክና የሕግ ጉዳዮች ላይ እየተካሄደ ያለው የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ ድርድር በመልካም ሁኔታ እየተካሄደ እንደሆነም አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

በሃገሮቹ መካከል መግባባትን ለመፍጠርና “የአፍሪካ ሃብት ጉዳይ በአፍሪካዊያን እንዲያልቅ” የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወደ አፍሪካ ኅብረት መምራቱን ኢትዮጵያ እንደምትደግፈው አምባሳደር ዲና ጠቁመው መተማመንን ለመፍጠርና በግርጌ ሃገሮች ላይ ጉዳት ሳይደርስ ውኃው ለጋራ ልማት ሊውል የሚችልበት መግባባት ለመድረስ ይቻላል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ተናግረዋል።

ሦስቱ ሃገሮች ስምምነት ላይ ለመድረስ አስበው የጀመሩት ንግግር በታለመለት ጊዜ ያልቃል ብለው እንደሚያስቡም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ገልፀዋል።


VOA Amharic 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ዘና ፈታ ከደሬ ጋር| ኮሜዲያን ልመንህ በሳቅ አፈረሰን!

Next Story

በኢትዮጵያ ውስጥ የተደረገውን ጀኖሳይድ ለአለም ለማሳወቅ እየሰራን ነው”-ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ

Go toTop