በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ስድስት ተጨማሪ ሰዎች ተገኙ

April 3, 2020

ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 74 ሰዎች ውስጥ 6 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።

ይህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 35 እንዳደረሰው የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡት ውስጥ አምስቱ ከአዲስ አበባ አንደኛው ደግሞ ከድሬዳዋ ሲሆን፥ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

በአዲስ አበባ ከተያዙት ውስጥ ሁለቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው የ35 ዓመት እና የ30 አመት ወንዶች ሲሆኑ፥ መጋቢት 10 መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም ከዱባይ የመጡ ናቸው ተብሏል።

ሁለቱም ዜጎች አስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት የገቡ መሆናቸውንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው።

ሶስተኛው የ28 ዓመት ወጣት፣ አራተኛው የ56 ዓመት ወንድ፣ አምስተኛው የ30 ዓመት ወንድ የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው።

ሰዎቹ ያላቸው ግንኙነት እየተጣራ መሆኑንም ተገልጿል።

ስድስተኛዋ ግለሰብ የ33 ዓመት ሴት ስትሆን በድሬዳዋ ከዚህ በፊት በኮሮና ቫይረስ መያዙ ከተገለጸው ሰው ጋር ግንኙነት የነበራት መሆኑም የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል ።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

ኤፍ ቢ ሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ለኢትዮጵያ ኮርናን ለመከላከል እቤታችሁ ተቀመጡ ከማለት ሌላ ዓማራጭ መታሰብ አለበት – ሰርፀ ደስታ

Next Story

የኮረና ቫይረስ ወረርሽን አደጋ እና የሀገርና ሕዝብ ደህንነት

Go toTop