ለአርቲስት ይሁኔ በላይ እና መሐሪ ደገፋው ሽኝት ተደረገ

December 26, 2018

እየተደረገ በነበረው ትግል በሙያቸው የወገናቸውን ድምጽ በማሰማት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱት አርቲስት ይሁኔ በላይ እና መሐሪ ደገፋው ወደ ኢትዮጵያ ሊያቀኑ ነው:: ይህን ተከትሎም ትናንት በዋሽንግተን ዲሲ በወዳጅ ጓደኞቻቸው አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል::

ይሁኔ እና መሐሪ ታህሳስ 27 2011 በጎንደር በአፄ ፉሲል ስታዲየም የመጀምሪያ የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ከዚያም በተለያዩ ከተሞች እየተዟዟሩ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል::

መሐሪ “እግዚአብሔር ይመስገን ከጀግና ህዝብ መሀል ልንገኝ ነው ነው እኔና ይሁኔ:: በDMV የምትገኙ እንዲህ ያማረ ሽኝት ስላረጋችሁልን ውለታችሁን እግዚአብሔር ይክፈልልኝ” ብሏል::
https://www.youtube.com/watch?v=HxjVbnkoygk

Previous Story

ፖሊስ የኮሎኔል ደሴ ዘለቀ ብርሃንን ጉዳይ ለአቃቤ ህግ አስረከበ::

Next Story

ለኢትዮጵያ ኢንቨንስትመንት ኮሚሽን ዳይሬክተር ጄኔራል ተሾመ

Go toTop