ፖሊስ የኮሎኔል ደሴ ዘለቀ ብርሃንን ጉዳይ ለአቃቤ ህግ አስረከበ::

December 25, 2018

በሌብነት ወንጀል ተጠርትረው የታሰሩት ኮሎኔል ደሴ ዘለቀ ዛሬ ፍድር ቤት ቀርበው መርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ ለአቃቤ ህግ ማስረከቡን ገለጸ::
ኮሎኔል ደሴ ዘለቀ ብርሃን የአዳማ እርሻ መሳሪያዎች ኃላፊ ሆኖ በሱማሌ ክልል ሀረዋና ኩለን በአፋር ክልል ደግሞ ሱሉታ መስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶች በሚሰሩበት ወቅት ከሌሎች ግብረአበሮች ጋር በመሆን የሙስና ወንጀል ድርጊቶችን በመፈፀም በፕሮጀክቶቹ አፈፃፀም ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ አድርጓል፣ ለአካባቢው አርሶአደሮች አገልግሎት የሚውሉ ትራክተሮች በህገወጥ መንገድ ግዢ እንዲፈፀም በማድረግ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ለራሳቸው እና ሌሎች ያልተገባ ጥቅም በማስገኘት እንደጠረጠራቸው መርማሪ ፓሊስ ለችሎቱ አስረድቷል። አቃቤ ህግም የክስ መመስረቻ 15 ቀን ጠይቆ ፍርድ ቤቱ 14 ቀን ፈቅዷል።

የኤፈርቱ መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተፈናቅለው በትግራይ ክልል ለሚገኙ የትግራይ ተወላጆች የ12 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ:: የኩባንያው ስራ አስኪያጅ አቶ ክብረዓብ ተወልደ፥ የተቋሙ እያንዳንዱ ሰራተኛ ከወርሃዊ ደመወዙ ከአምስት እስከ 20 በመቶ በማዋጣት ከ560 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል::
ሕወሓት መሰቦ ሲሚንቶ በኢትዮጵያ ያለውን የሲሚንቶ ገበያ እንዲቆጣጠረው በተለያየ አሻጥር ታላቁን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካን ማምረት እስኪያቅተው ድረስ ሲያዳክም መቆየቱ የሚታወስ ነው::
https://www.youtube.com/watch?v=JAP5FStPHSY&t=3s

Previous Story

የቀድሞው የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባና ምክትል ከንቲባ በሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ

Next Story

ለአርቲስት ይሁኔ በላይ እና መሐሪ ደገፋው ሽኝት ተደረገ

Go toTop