በወልቃይት በሚገኘው ጎሮ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይማሩ የነበሩ የአማራ ልጆች ዘንድሮ እንዳይመዘገቡና እንዳይማርሩ መከልከቸውንና ይህንንም እንደሚያወግዝ የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ (አወጋን) ገለጸ። ልቻቸው እንዳይማሩ የተከለክሉባቸው ወላጆች ጉዳዩን በአካባቢው ወደሚገኝ የመንግስት አስተዳደር አቤት ማለታቸውንና በስፍራው ካሉ የመንግስት አካላትም “ይህ የትግራይ እንጅ የአማራ አገር ባለመሆኑ ትምህርት ቤቱ የአማራን ልጆች አለመቀበሉ ተገቢ ነው” የሚል ምላሽ ማገኘታቸውን አወጋን ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ ገልጿል። ይህን መረጃ ይዛ ዘ-ሐበሻ ከመንግስት አካላት ለማረጋግጥና የነርሱን ምላሽ ለማካተት ያደረገችው ጥረት አልተሳካም።
ወልቃይት ከጥንት ከጠዋት ጀምሮ የጎንደር ክ/ሃገር ግዛት የነበረ ቢሆንም አሁን ግን የትግራይ ነጻ አውጭ ቡድን የትግራይን ግዛት ለማስፋፋት ካለው ገደብ የለለው ህልሙ በመነሳት ባለእርስት የሆነውን አማራ በሃይል በማፈናቀልና በማጥፋት ከ500,000 በላይ የትግራይን ተወላጆች ተከዜን አሻግሮ አስፍሮበት እንደሚገኝ የገለጸው አወጋን በተማሪዎቹ የትምህርት ክልከላ ዙሪያ ያወጣውን መግለጫ እንደሚከተለው አስተናግደነዋል።
ከአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ ( አወጋን ) የተሰጠ መግለጫ
በወልቃይት እና ፀገዴ ቅሪት አማራ ተወላጆች ከትምህርት መታገድን አጥብቆ ያወግዛል !!!
ዘረኛው እና ወራሪው በወረራ ከያዘው እና ከ500 000 በላይ ሰፋሪዎችን ካሠፈረበት የወልቃይት አካባቢ የሚገኙ ቅሪት የአማራ ተወላጆች ልጆች ዛሬ ለምዝገባ ወደ ትምህርት ቤት ሂደው እሄ የትግሬ እንጂ የአማራ ሀገር ስላልሆነ እዚህ መማር አትችሉም ተብለው አምሮን በሚነካ እና ዝቅ በሚያደርግ ንግግር ህፃኖቻችን እያለቀሱ ተመልሰዋል።
የተማሪዎች ቤተሰቦች በፍጥነት ባካባቢው ለሚገኘው የትምህርት ቢሮ አቤት ቢሉም የተሰጣቸው መልስ ለልጆች ከተነገረው በከፋ ነው።
አወጋን ይህን እኩይ ተግባር አጥብቆ የሚቃወም ሲሆን ባስቸኳይ መልስ እንዲሰጣቸው እና ልጆች ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ አጥብቆ ያሳስባል።
መንግስት ይሄን ለማድረግ ቢዘገይ የኛ ምላሽ ፈጥኖ ይደርሳል !!!
የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ (አወጋን)