ድምፃዊ ኢዮብ መኮንን በጠና ታሟል

August 16, 2013

(ዘ-ሐበሻ) ታዋቂው ድምፃዊ እዮብ መኮንን በጠና መታመሙ ታወቀ። ድምፃዊው ኢዮብ መኮንን በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኝ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል።
ከኢትዮጵያ ምርጥ የሬጌ ሙዚቃ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የህፕነው ኢዮብ መኮንን በአሁኑ ወቅት “ኮማ” ሊባል በሚችል ደረጃ ላይ እንዳለ ያስታወቁት ዘጋቢዎች አድናቂዎቹ ሕይወቱ እንዲተርፍ በመጸለይ እንዲተባበሩ ጥሪ ቀርቧል። በኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ በተለይ የራሱን መንገድ በመከተል “እንደቃል” የተሰኘውን የበኩር ሲዲውን ያቀረበው ኢዮብ መኮንን የበሽታው ዓይነት እስካሁን ባይታወቅም ህመሙ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ አድናቂዎቹ ወደ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በመትመም ላይ እንደሆኑ ታውቋል።
በመጀመርያ አልበሙ በብዙ አድማጮች ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘው እና እስከ አሁንም እንደ አዲስ እየተደመጠለት ያለው ኢዮብ መኮንን ከህመሙ አገግሞ ወደ ሥራው እንዲመለስ ዘ-ሐበሻ መልካሙን ሁሉ ትመኛለች።

የሚያያዝ ባይሆንም፦
ሸዋንዳኝ ኃይሉ ስለክህደት የዘፈነውን አዲስ ስታይል ዘፈን ለማድመጥ እዚህ ይጫኑ፡

http://www.youtube.com/watch?v=iwrAJ1DkPxQ

አቤል ቤተስላሴ የተባሉ ሰው በፌስቡክ ገጻቸው ስለኢዮብ ሁኔታ እንዲህ ጽፈዋል።
ማክሰኞ ነሀሴ 7, 2005 ዓ.ም ረፋዱ ላይ ሰውነቱን ለማሟሟቅ ሁሌም የሚያሽከረክራትን ብስክሌት ይዞ ከቤት የወጣዉ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ፍፁም ልዪ የሆነ የሬጌ ስልት ይዞ የመጣው አስደማሚ የድምፅ ቃናን የተላበሰው ድምፃዊ እዮብ መኮንን ወደቤቱ መመለስ እንደመሄድ ቀላል አልሆነለትም።
መኖሪያ ቤቱ መግቢያ ላይ ሲደርስ “አንድ እግሬ እምቢ አለኝ እስቲ ጫማ አውልቁልኝ” አለና ተዝለፈለፈ። ቤተሰቦቹም አፋፍሰው ወደ ሀያት ሆስፒታል ወሰዱት። እዮብ ግን መናገር እየተሳነው ነበር። ሀያት ሆስፒታል ወደ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ላካቸው። አሁንም ግን እዮብ መናገርና እራሱን መቆጣጠር እያቃተው ነበር። የቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች እዮብን ተቀብለው “አዲስ ያስገባነዉ ነው” ባሉት አየር መስጫ መሳይ ማሽን ላይ በማስተኛት እዮብን ለማንቃት ጥረታቸውን ጀመሩ። ግን እስካሁን አልተቻላቸውም። እዮብ እስካሁን ድረስ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ሪከቨሪ ውስጥ እራሱን እንደሳተ በማሽን መተንፈሱን ቀጥሏል።
በሆስፒታሉ ውስጥ የሚገኘው እያንዳንዱ ሰው በደቂቃዎች ክፍልፋይ የመንቃቱን ዜና ይጠባበቃል።
የበሽታውን መንስኤ ይኼ ነው ለማለት ባያስደፍርም ከደም ግፊት ጋር የተያያዘ ድንገተኛ የልብ ድካም (Heart Stroke) ሊሆን የሚችል ይመስለኛል ምክንያቱም በተመሳሳይ ህመም ያጣሁት የቤተሰብ አባል አለኝ እና ነው።
ህክምናውን በተመለከተ ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ ከሀኪሞች ጋር በምክክር ላይ የሚገኙ ሲሆን የተሻለ ነው ወደተባለው የኮሪያ ሆስፒታል ሄደውም ባደረጉት የመረጃ ልውውጥ ወደ ባንኮክ እንዲሄድ ምክር የሰጡ ቢሆንም ለዚህ የሚሆነው ወጪም ከወዳጆቹ የተሰበሰበ ሲሆን ሆኖም ግን አሁን ጉዳዩን እየተከታተሉ ያሉት ሀኪሞች ባለበት ሁኔታ መንቃቱን መጠባበቅ የተሻለ አማራጭ መሆኑን በመምከራቸው አሁንም እዛው ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ይገኛል።
በእያንዳንዷ ደቂቃ ፈጣሪ ድንገት እንዲያነቃው እና የእግዚአብሄርን ፍቅር እና ምህረት ይበልጥ የሚረዳበት እና አምላኩን የሚያገለግልበት አጋጣሚ ይሆንለት ዘንድ ሁላችንም አጥብቀን እንፀልይለት።

Previous Story

የኢትዮጵያ ጠላቶችና የአምላክ እጆች – አበራ ሽፈራው

Next Story

የአላሙዲ ፌደሬሽን የኢትዮጵያውያኑን ፌዴሬሽንን የገነጠሉትን ከአመራርነት አባረረ

Latest from Same Tags

የአብርሃ ደስታ የሰሞኑ ምርጥ ዘገባዎች

የህወሓት የኮብልስቶን ፖለቲካ (መቐለ) ======================== የመቐለ ወጣቶች (የዩኒቨርስቲ ምሩቃን) ተደራጅተው በኮብልስቶን ስራ ለመሳተፍ ቢወስኑም የህወሓት መንግስት ሊያስሰራቸው እንዳልቻለ ገለፁ። ወጣቶቹ በኮብልስቶን ስራ ተሰማርተው ስራ

ሁሉም ይናገር ሁሉም ይደመጥ!!

ከአንተነህ መርዕድ እምሩ በድሮ አጠራሩ ሻንቅላ በአሁኑ የጉሙዝ ብሄረሰብ የተማርሁት ትልቅ ነገር አለ። “በትልቆች ጉዳይ ምን ጥልቅ አደረገህ” እየተባልሁ በሚያሸማቅቅ ባህል አድጌ በጉሙዝ ህብረተሰብ
Go toTop

Don't Miss