የፎቶ ምንጭ ከAESAONE ድረገጽ
(ዘ-ሐበሻ) በሼህ አላሙዲ የሚመራውና ራሱን AESAONE በሚል የሚጠራው ፌዴሬሽን አዳዲስ የቦርድ አመራሮችን መረጠ። ዘንድሮ ዋሽንግተን ዲሲ በተደረገው የአላሙዲ የስፖርት ፌስቲቫል በሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ቦይኮት ተደርጓል የሚባልለት የአላሙዲ የስፖርት ፌስቲቫል ባዶ ስታዲየም ታቅፎ ውድድሩን ለማከናወን መገደዱ መዘገቡ ይታወሳል።
በሰሜን አሜሪካ ላለፉት 30 ዓመታት ኢትዮጵያውያኑን በመወከል በየዓመቱ ሲያስተባበር የነበረውን ESFNA ለሁለት ለመክፈል በመሞከር ለአላሙዲ ታማኝነታቸውን ያሳዩት ሰዎች በሙሉ በአዲሱ አመራር ውስጥ ያልተካተቱ ሲሆን ይህ የሆነበትም ምክንያት ባለፉት 2 ዓመታት የሃብታሙ ሰውዬ ሚሊዮን ዶላር ቢፈስም የአንዱንም ኢትዮጵያዊ ቀልብ ሊገዛ ባለመቻሉ እንደሆነ ታዛቢዎች ያላቸውን አስተያየት ይሰጣሉ።
በሼህ መሀመድ አላሙዲን የሚደገፈው ፌዴሬሽንን ለመምራት የተመረጡት አዳዲስ አመራሮች፡
1ኛ. ቴዎድሮስ ፈቃደ (ከዲሲ)
2ኛ. አክሊሉ ግደይ (ከአትላንታ)
3ኛ. አንዱ ደበበ (ከሚኒሶታ)
4ኛ. መሳይ አምበርብር (ከዲሲ) መሆናቸው ታውቋል።
ዘንድሮ ሼህ መሀመድ አላሙዲ ያረፉበት ሆቴል ሳይቀር ኢትዮጵያውያኑ በመሄድ ከፍተኛ ተቃውሞ እንዳሰሙባቸው መዘገቡ ይታወሳል።