ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ጦርነት ምክንያት እያሽቆለቆለ የሄደው የአውሮፓ አገራት መገበያያ ገንዘብ ዩሮ ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዶላር በታች ወረደ።
ሩሲያ የአውሮፓን የሃይል አቅርቦት ልትገድብ ትችላለች የሚለው ፍራቻ ዩሮን እንደ መገበያያ ገንዘብ በሚጠቀሙ አገራት (ዩሮ ዞን) እንዲወርድ እድሉን ጨምሯል።
የአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክ ሌሎች ማዕከላዊ ባንኮች የመገበያያ ገንዘቡን የምንዛሬ ዋጋ ጭማሬ እንዲያዘገዩ ማድረጉን ተከትሎም ዩሮን የበለጠ አዳክሞታል ተብሏል።
ማዕከላዊ ባንክ የመገበያያ ገንዘቡን የምንዛሬ ተመን ምጣኔ ሲጨምር አለምአቀፍ ኢንቨስተሮች ዋጋ ያላቸውን ንብረቶች በዚያ ገንዘብ ለመያዝ ያላቸው ፍላጎት ስለሚጨምር ምንዛሬዎችም ይጨምራሉ
BBC