ፀሀይ ውጪ ውጪ! – ገለታው ዘለቀ

July 13, 2022

ጎህ ሳይቀድ ማለዳ የአማሮች መርዶ

ጎህ ሳይቀድ ማለዳ የትግራዋይ መርዶ

ደግሞ ማልዶ ማልዶ የኦሮሞ መርዶ

ደግሞ ማልዶ ማልዶ የኮንሶዎች መርዶ

ደግሞ ማልዶ ማልዶ ያገሬ ልጅ መርዶ

አዘን ደረበባት ኢትዮጵያ አይኗ ጠፋ

ልቧ ተሰበረ ውሰጥ አንጀቷ ከፋ

በቃ በይ እባክሽ ፀሀይ ውጪ ውጪ

የመልካሙን ዜና እቅፍ ነዶ አምጪ

ጎህ ቅደጂ ፀሀይ አ’ዋፍት አሰማሪ

የደስታን ዜና የሰላም አዝማሪ

ማልዶ መርዶ ቀርቶ የሀሴት ሆኖለት

አበሻ በሙሉ እንጀራ ይውጣለት….. ሰላም ይሁንለት…. ደሰታ ይሁንለት…..

እባክሽን ፀሀይ ዛሬ ለታ ውጪ

እባክሸን ፀሀይ

እባክሽ እባከሸ

እባክሽን ሰልሽ?

ሀምሌ 7 ቀን 2014

ገለታው ዘለቀ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

በጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ በማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አመራሮችና ሰራተኞችን ዝርዝር ይፋ አደረገ

Next Story

ዩሮ በ20 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዶላር በታች ወረደ

Go toTop