በቄለም ወለጋ ትናንት ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም. የተፈፀመው ጥቃት አድማሱን በማስፋት፣ ከመንደር 20 ወደ መንደር 21 ተዛምቷል።
ከጭፍጨፋው ተርፈው ወደ ሌላ አካባቢ የሸሹ የአካባቢው ኗሪ እንደገለፁት ሕፃናት፣ ሴቶችና አዛዎንቶችን ጨምሮ ቁጥራቸው በትክክል ያልታወቀ ሰዎች ዛሬም በመንደር 21 ተገድለዋል። ዛሬ ከተጨፈጨፉት መካከል የአርጎባ ማሕበረሰብ ተወላጆችም (በኦነግ/ሸኔ አማራ ነው የሚባሉት) ይገኙበታል።
ኦነግ-ሸኔ ጭፍጨፋውን ከኦሮሞ ልዩ ኃይል ጋር በመናበብ እንደፈፀመውም የአካባቢው ኗሪዎች ተናግረዋል። ታጣቂው ቡድን ወለጋን ከአማራ ብሎም ኦሮሞ ካልሆኑት ሁሉ ለማፅዳት እየሠራ መሆኑንም ከጭፍጨፋው የተረፉ አማሮች ተናግረዋል።
ጨፍጫፊው ኃይል ዘመናዊ የቡድን መሳሪያዎችን ጭምር የታጠቀ እንደሆነም ገልፀዋል።