የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጮች ዛሬ የምክር ቤቱን መደበኛ ስብሰባ አቋርጠው እንደወጡ በምክር ቤቱ የአብን ተወካይ ደሳለኝ ጫኔ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል። የፓርቲው ተወካይ ደሳለኝ ጫኔ ምክር ቤቱ በመደበኛ አጀንዳዎች ላይ ከመወያየቱ በፊት፣ ምክር ቤቱ በኦሮሚያ ክልል እና በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ እየተፈጸሙ ባሉ ጅምላ ጭፍጨፋዎች እና የዘር ማጽዳት ወንጀሎች ላይ በቅድሚያ እንዲወያይ አጀንዳ እንዲያዝላቸው የምክር ቤቱን አፈ ጉባዔ መጠየቃቸውን አብራርተዋል።
ሆኖም የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ ምክር ቤቱ ቀደም ብሎ ባልተያዘ አጀንዳ ላይ ሊወያይ እንደማይችል ገልጸው ጥያቄውን ስላልተቀበሉት፣ ራሳቸውን ጨምሮ በምክር ቤቱ የፓርቲው ተመራጮች ስብሰባውን አቋርጠው መውጣታቸውን ደሳለኝ ገልጸዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው መደበኛ ስብሰባው ለውይይት የያዘው አጀንዳ፣ የፌደራል መንግሥት መስሪያ ቤቶችን የ2013 ዓ፣ም በጀት ዓመት ሒሳብ፣ የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲት እና የክንውን ኦዲት ሪፖርቶችን ማዳመጥ እና መወያየት ነው። የፌደራል መንግሥት ኦዲት ሪፖርቶችን ለምክር ቤቱ ያቀረበው ፌደራል ዋና ኦዲተር ነው።
[ዋዜማ ራዲዮ]
——————-
“….በህይወቴ እንደዚህ የአራጅ ዘመን ላይ እንደርሳለን ብዬ አላስብም ነበር። በህግ ማስከበር ስም ብዙ ሰው ተለቀመ፣ ገዳይ ግን በነፃነት ያርዳል..!!!”
ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀፀላ …
ሁልህም ንቃ ፋኖ አሳዳጁ ኦሮሙማ በግላጭ ዘር እያጸዳ ነው፤መፍት ሄው ዓይንን ላወጣ ዓይኑን መመንገል ብቻና ብቻ ነው…።