“ሱቅ እየገቡ ዕቃ ይሰርቃሉ የሚል የፌዝ ክስ በማቅረብ የጦር ብርጌዱን የአማራ ፋኖ ላይ ያለሃፍረት ያዘመተው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፣ ዘመነ ካሴን ለመያዝ በምድር አንድ ክፍለጦር ያዘመተ እና በሰማይ የጦር ድሮኖቹን ለሰዓታት በጎጃም ሰማይ ላይ እንዲበሩ ያደረገ ጠቅላይ ሚኒስትር ፣ ሕወሓት ጋር በተደረጉ ውጊያዎች የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት ጭምር ሙሉ ለሙሉ እንዲቋረጥ ለማድረግ መወሰን የደፈረ ጠቅላይ ሚኒስትር ፣ በሶማሌ ክልል አብዲ ኢሌ ላይ እና በደቡብ ክልል ወላይታ ላይ ፈጣን እርምጃ ለመውሰድ የወሰን ጠቅላይ ሚኒስትር በየዕለቱ ዘግናኝ የሆኑ ግድያዎች የሚፈፀምበት ኦሮሞ ክልል ላይ መጨከን እና የማያዳግም እርምጃ መውሰድ እንዴት ተሳናቸው ? ኦሮሞ ክልል ሲሆን ለምን ያመነታሉ ?”
ብሎ ይጠይቃል፡፡ እርምጃ ለመውሰድ ያመነታ አይመስለኝም፡፡ እርምጃ ለመውሰድ ሞክሯል፡፡ ነገር ግን ፡
1ኛ እርሱ መንግስት ውስጥ ፣ ደህንነት መስሪያ ቤት፣ መከላከያ ውስጥ ፣ እንዲሁም የኦሮሞ ክልል ልዩ ኃይል ውስጥ ኦነጎ አሉበት፡፡ እንቅስቃሴ ለማድረግ ሲወሰን፣ ኦነግ አስቀድሞ መረጃ ይደርሰዋል፡፡ ስለዚህ የአብይ መንግስት ራሱን ኦነግ ስለሆነ፣ ራሱን ማሸነፍ አልቻለም፡፡ ጦርነትን የሚወስደው ደግሞ በዋናናነት ወታደራዊ መረጃ ነው፡፡
2ኛ የወታደራዊ አመራር ብቃት የለውም፡፡ ማውራት እንጂ የጦር ስትራቴጂ አያውቅም፡፡ አንዴ አቁሙ ይላል። አንዲ ቀጥሎ ይላል፡፡ የርሱ የጦር አዝማችነት ታች ያሉ መኮንኖችም ግራ ያጋባበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
3ኛ የፖለቲካ ውሳኔዎቹ ህዝቡን የሚያቅፍ ሳይሆን የሚገፋ፣ አምባገነናዊ በመሆኑ፣ ወጣቶችን ማሰር፣ ማወክ፣ ማሸበር ስለበዛ ነው፡፡ ኦህዴድ ከሕወሃት የባሰ አፋኝ ስለሆነ፣ ኦነግ አራት እጥፍ ጭራቅ ቢሆንም፣ ብዙ ተከታዮችን ለማግኘት ችሏል፡፡ በወለጋ በተለይም በርካታ የወረዳና የዞን አመራሮች ሁለት ኮፍያ ያላቸው ናቸው፡፡ ቀን ቀን የኦህዴድን ኮፍያ ያደርጋሉ፣ ማታ ማታ የኦነኝ ኮፍያ ያደርጋሉ፡፡ አብይ በፖለቲካው ረገድ የሕወሃት ሶስት እጥፍ አፋኝ መሆኑ ቀርቶ ህዝቡን ቢያከብር ኖሮ፣ ኦነግ የትም አትደርስም ነበር፡፡