የማስረሻ ሰጤ ወንድም በመያዣነት ተይዞ እየተሰቃየ መሆኑ ተገለፀ!!

June 5, 2022
 6 የማስረሻ ሰጤ ቤተሰቦች እየተሳደዱ እና ከፊሎቹ ደግሞ በእስር ቤት እየተሰቃዮ ናቸው!!
የማስረሻ ሰጤ ወንድም በመያዣነት ተይዞ እየተሰቃየ መሆኑ ተገለፀ!! በተጨማሪም፣ የአቶ ሰጤ ቤተሰቦች ዛሬ የማስረሻን ወንድም ለመጠየቅ ሄደው በወጡበት ታፍነው ቀርተዋል።
የመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤን አባት ለመያዝ እየፈለጓቸው እንደሆነም ነው ቤተሰቦቻቸው የሚናገሩት። እህቱንም በአሁኑ ሰዓት እያሳደዷት እንደሆነ ታውቋል።
በአጠቃላይ 6 የማስረሻ ሰጤ ቤተሰቦች እየተሳደዱ እና ከፊሎቹ ደግሞ በእስር ቤት እየተሰቃዮ መሆኑ ታውቋል።
ባሳለፍነው ረዕቡ ዕለት በመያዣነት እስር ቤት የገባው ወንድሙ ቢተው ሰጤ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞበታል።
እስር ቤት ቢተው ሰጤን ለመጠየቅ የተጓዙ ሁለት ጎረቤቶቹም በሄዱበት ተይዘው ታስረው እየተንገላቱ መሆኑ ታውቋል።
ዘገባው—-ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የተቃዋሚ ፓርቲዎች የምክክር ቤት (caucus) ተቋቋመ

Next Story

የአራት ኪሎው አድባር – ተመስገን ደሳለኝ!

Go toTop