![](https://amharic.thehabesha.com/wp-content/uploads/2022/03/hewan.jpg)
ሄዋን ከ2008 ዓ ም ጀምሮ ከፋኖ አማራ ጋር አባል ሁና የታገለች የተሰጣትን ተልኮ ሁሉ በአግባቡ የፈፀመች ኢትዮጵያዊን በማዳን እንቅስቃሴ ግንባር ቀደም ጀግና እህታችን ነበረች።
ሄዋን ሁሌም ወደ ማታ ብቻዋን ቤተክርስቲያን የመሳለም ልምድ አላት። በትናትናው ዕለትም አዲስ አለም አካባቢ በሚገኘዉ መስቀለ እየሱስ ቤተክርስቲያን ልታሰለም እንደወጣች ማንነታቸው ባልታወቁ ሰወች ተገላ ተገኝታለች።
በጣም ያሳዝናል በጦርነት ሳትሞት መንግስት ባለበት ሀገር ሀገር ሰላም ብላ ቤተክርስቲያን ለመሳለም በሄደችበት በአደባባይ ተገድላለች
በተደጋጋሚ በመላው አማራ ክልል በከፍተኛ ደረጃ ፋኖዎች እየተገደሉ ነው ! እየሞቱ ሀገር ባዳኑ ምላሻቸው ይህ መሆኑ በጣም ያሳዝናል ! አይ ኢትዮጵያ
እህታችን ነብሷን በአፀደ ገነት ያኑርልን
ከ አፈትላኪ ዜናዎች የተገኘ