የኤርትራው የደህንነት ክንፍ ያወጣው መረጃ ነው ። እንዲህ ተተርጉሟል

February 3, 2022

debre1

” ልጆቻችሁ አልተመለሱም ፤ ስለ ደህንነታቸውም አናውቅም”

ትህነግ ከተጠያቂነት ለመዳን በምታደርገው እረፍት የለሽ ያልተቋረጠ ሩጫ፤ ዛሬ በይፋ የ300,000 (የሦስት መቶ ሺህ ) የትግሬ ወጣቶች በህይወት ስለመኖራቸው ማረጋገጫ እንደሌላት በይፋ አስታውቃለች ። በውል ስምና አድራሻቸው ሳይሰነድ በጦርነት መሃል እያስገባች ወደ እልቂት የማገደቻቸው የትግሬ ወጣቶች ፤ ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ በ1991 በትህነግ ታጋዮች ላይ እንዳደረገችው

” ልጆቻችሁ ካልተመለሱ መስዋእት እንደሆኑ ቁጠሯቸው”

በሚል የንቀት መግለጫ እንደሰጠችው ሁሉ አሁንም ያለው አዝማሚያ ያን ይመስላል የሚል አቅጣጫ ተሰጥቷል ።

የትህነግ አመራር ጥቅምት 24 በሰሜን ዕዝ ላይ በፈፀመችው ጭፍጨፋ ምክንያትነት የተለኮሰው ጦርነት የትግሬ ህዝብ ላይ ይሄ የማይባል መዓት እንዲወርድበት አድርጋለች ።ከትግሬ ህዝብ ፍቃድና ይሁንታ ውጪ የተለኮሰው ጦርነት ፥ አሁን ላይ ትግራይን ፍፁም አውድሟታል ።በሚሊየን የሚቆጠር ትግሬን ለስደት ዳርጓል፥ ረሃብና የመድኃኒት እጥረትም አንግሷል ፥ የትግሬ ህዝብ በታሪኩ አይቶም ሰምቶትም የማያውቅ መከራና ውድመት ቆሞ እንዳያይ ሆኗል ።

በጣም የሚያሳዝነው የትግሬን ወጣት በማስገደድ በደ ጦርነት አስገብታ እንዲቀቀል ስታደርግ የከረመችው ትህነግ ፥ ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ከ200,000 ( ከሁለት መቶ ሺህ ) በላይ የትግሬ ወጣቶች ወደ ጦርነት ማግዳ አስጨርሳቸዋለች ። ከጥቅምት 24 ጀምሮ ያስጨረሰችው የትግሬን ወጣት በተጨማሪ ከግምት ውስጥ ስናስገባ በድምሩ

1/2 (ግማሽ ሚሊየን ) የሚደርስ የትግሬ ወጣት በእሳቱ ተበልቷል ። በዌቭ ታክቲክ (በህዝብ ማዕበል የጦር ስልት ) የትግሬን ወጣት ወደ ጦርነት ስትቀቅላቸው የከረመችው ትህነግ ዛሬ ላይ ቁጥራቸውን ቀንሳ ወሬያቸው ጠፋኝ ስትል በይፋ ማመኗ በትግሬ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን የስነ-ልቦና ስብራት ጥልቀቱን መገመት ይቻላል ።

ከ100,000 (ከመቶ ሺህ ) በላይ ተወጣቶችን ሬሳ በሲኖ ትራክ መኪኖች እያጓጓዘች በትግሬ ምድር በጅምላ ስተቀብር ቆይታለች ። ከአምሓራ እና ከአፋር ክልሎች ሲሰበሰብ የከረመው ሬሳ በትግሬ ላይ “የዘር ማጥፋት ” ተፈፅሟል በማለት ለተፈለገውን የፖለቲካ ጨዋታ እንደ ግብአት በመጠቀም ለማዳመቂያነት እንዲበቃ ነበር ሬሳ ስትጎትት የነበረችው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ፈንታሌ ውስጥ ስለተፈፀሙት ግድያዎች ኢሰመኮ ሪፖርት አወጣ

Next Story

ቤቴ ድረስ መጥተው አስፈራሩኝ – አስቴር በዳኔ ዘ-ኢትዮጵያ

Go toTop