“አገር ለማፈራረስ ለመጣ አሸባሪ የተሰጠው ምላሽ ለዘላቂ ሰላም መፍትሔ ነው” ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

December 8, 2021
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አገርን ለማፈራረስ ለመጣው አሸባሪ ኃይል እንዳመጣጡ የተሰጠው ምላሽ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ መፍትሔ መሆኑን ገለጹ።
በአገሪቱ ላይ ከውስጥና ከውጭ የመጣውን ጫና ኢትዮጵያዊያን በህብረት እየመከቱት ይገኛልም ነው ያሉት፡፡
የዘንድሮው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ሲከበር በተለያዩ ዘርፎች ለአገሪቱ እየተዋደቁ ለሚገኙት ዜጎች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
በድሬዳዋ እተከበረ በሚገኘው በዓል ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንቷ ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ ሰላምን ለማስፈን የሚደረገው ጥረት ቀዳሚውን ቦታ እንደሚሰጣውም አሳውቀዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው ብዝኃነት ለአገራችን ማጌጫ እንጂ መጋጫ (መጣያ) መሆን የለበትም ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በምንም ምክንያት የማንንም ጣልቃ ገብነት አይፈልጉም፤ በታሪክም አያውቁም ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡፡
ዘገባው የዋልታ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የአማራ ሕዝባዊ ኅይል (ፋኖ)፣ የምስራቅ አማራ ፋኖ፣ የአማራ ሚሊሻ፣ እና የአማራ ልዩ ኃይል የጣና ብርጌድ ጥምር ኃይል

Next Story

መሞቻ ስንኞች ገጣሚ ሐዋዝ የሻነህ

Go toTop