የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የቀረቡትን የምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ እና ምክትል ከንቲባ ሹመቶችን አፀደቀ

September 28, 2021

addis ababa2

አዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤቱ ያቀረቧቸው የምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ፣ ረዳት ተጠሪ እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የተለያዩ ቢሮዎች ኃላፊዎችን ምክር ቤቱ ተቀብሎ አፅድቋል።
ምክር ቤቱ ሹመቱን በ125 ድጋፍ እና በ2 ድምፀ ተአቅቦ ነው ያፀደቀው።
ኃላፊነቱን የተቀበሉት 8 አዳዲስ ተሿሚዎች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል
1- አቶ መለሰ አለሙ፦ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ
2- አቶ ጃንጥራር አባይ፦ ምክትል ከንቲባ እና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
3- ወ/ሮ ነጂባ አክመል፦ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ
4- አቶ ጥራቱ በየነ፦ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ
5- ወ/ሪት ያስሚን ውሀቢ፦ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ
6- ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን፦ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ
7- አቶ አለማየሁ እጅጉ፦ የመንግስት ረዳት ተጠሪ
8- አቶ ተተካ በቀለ፦ የመንግስት ረዳት ተጠሪ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩን አስፈፃሚ አካላት መልሶ ለማደራጀት በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ በካቢኔ ደረጃ የተደራጁ ተቋማት ዝርዝር ይፋ ሆኗል፡፡
የተቋማቱ ዝርዝርም እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
1. ከንቲባ
2. ምክትል ከንቲባ
3. የከተማ ስራ አስኪያጅ
4. የስራ፣ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
5. የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ
6. የፋይናንስ ቢሮ
7. የሰላም ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ
8. የፍትህ ቢሮ
9. የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
10. የትራንስፖርት ቢሮ
11. የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ
12. የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ
13. የስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ
14. የንግድ ቢሮ
15. የጤና ቢሮ
16. የትምህርት ቢሮ
17. የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
18. የባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ
19. የገቢዎች ቢሮ
20. የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
21. የኮሚኒኬሽን ቢሮ
22. የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ
23. የፕላንና ልማት ኮሚሽን
24. የኢንቨስትመንት ኮሚሽን
25. እንደ አስፈላጊነቱ በከንቲባ የሚሰየሙ ሌሎች የካቢኔ አባላት እንደሚኖሩ ከከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
(ዋልታ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

❝ባለቤቴን ማክሰኞ ገድለውት እስከ ቅዳሜ አልጋ ላይ አስተኝቼ ሰነበትኩ❞

Next Story

‹‹ሸኔ አሸባሪው ህወሓትን ወደ ስልጣን የመመለስ እንጂ ወደ ጫካ የሚወስድ የኦሮሞ ጥያቄ የለውም››

Go toTop