❝እነርሱን ቀርቶ እነርሱን መሰል ቡድን በኢትዮጵያ ምድር ዳግም እንዳይበቅል መሥራት ይገባል❞ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

September 16, 2021
242115530 1634560976718890 8446469509555246963 nከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው እና ለወገናቸው ቀናዒ ልቦናን የታደሉ ስለመሆናቸው የሀገር ውጭ ጸሐፍት ሳይቀር በድፍረት ይናገራሉ፡፡ ስለሀገራቸው ክብር፣ ስለወገናቸው ፍቅር ሲሉ የማይወጡት ተራራ፣ የማይወርዱት ሸለቆ፣ የማያሳልፉት መከራ እና የማይቀበሉት መራር ተጋድሎ አልነበረም፡፡ ከስንዴ መካከል እንክርዳድ፣ ከአበባ መካከል እሾህ ተፈጥሯዊ የመሆኑን ያክል እነዚህኞቹ እንደዚህ የበቀሉ ናቸው፡፡ የሽብርተኛው ትህነግ ቡድን አባላት ከኢትዮጵያውያን ደጋግ ልቦች መካከል የበቀሉ እርጉማን አረሞች ናቸው፡፡

በየዘመኑ እልፍ አዕላፍት ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ትጉሃን የመሆናቸውን ያክል ጥቂት ሰነፎችም አይጠፉም፡፡ በየዘመናቱ ስለሀገራቸው ክብር በሠሩት ገድል ስማቸው ከፍ ብሎ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚወሳላቸው እንዳሉ ሁሉ ደማቁ የኢትዮጵያ የነፃነት ታሪክ በጥቁር ያቀለማቸው አበያዎች እና ባንዳዎችም ነበሩ፡፡ የሽብርተኛው ትህነግ ቡድን አባላት በእርግጥም የዚህ ዘመን የኢትዮጵያ አበያዎች ናቸው፡፡

በሴራ ተዘርተው በክህደት የበቀሉ፤ በቂም ተጸንሰው በጥላቻ የተወለዱ፤ በልዩነት በቅለው በክፍፍል ያደጉ፤ ብቻቸውን በልተው እልፍ ሆኖ መሞት የሚሻቸው፤ ለራሳቸው ያልበቁ ለሌሎችም የማይተርፉ ናቸው፡፡ መዓዛቸው ሀሴት አልባ፣ የተናገሩት የማያምር፣ ከአንድነት ይልቅ ልዩነት፣ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻ፣ ከእምነት ይልቅ ክህደት፣ ከአብሮነት ይልቅ መነጣጠል እና ከሚያሻግር ድልድይ ይልቅ የልዩነት ግንብ ማቆም የሚቀናቸው ሆነው ተፈጥረዋል፡፡

በንስሃ ዘመናቸው እንኳን ከአርምሞ ይልቅ ዳንኪራ እና ሁካታ ቀንቷቸው ብቻቸውን መውረድ ሲገባቸው ሀገር እና ትውልድን አብረው ሊያወርዱ ሲዳዱ አይተናል፡፡

ከፍ ያለችውን ሀገር ለማውረድ፣ ውጋግራ ለመነቅነቅ እና ማገር ለማላቀቅ በእርጅና ዘመናቸው ሲበረቱ ላየ እውነትም እነዚህን የገንጣይ አስገንጣይ ቡድኖች ኢትዮጵያውያን ናቸው ብሎ ለመጥራት ምን ያክል እንደሚከብድ ይረዳል፡፡ሰዎቹ ከመመረቅ ይልቅ ለመረገም ተፈጥረዋል።

በሠሩት ግፍ የኢትዮጵያውያን አንድነት እየታየ ነው የሚሉት ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ብረት የሚቀጠቀጠው እንደጋለ ነውና በዚህ ወቅት የቀጣዩን የኢትዮጵያ መንገድ በውል ማበጀት ይገባል ብለዋል፡፡

አሁን የታየውን ሀገራዊ አንድነት በዚህ ፍጥነት ማምጣት ይከብዳል የሚሉት ዲያቆን ዳንኤል፤ አዲሱ ትውልድ በየወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶቹ የኢትዮጵያ ስም ሲነሳ ሲያነባ ከማየት በላይ ምን ሌላ ተዓምር ይጠበቃል ይላሉ፡፡

የሽብርተኛው ትህነግ አባላት ወደ ስልጣን እርካብ ሲመጡ ኢትዮጵያን ያሳጧትን አንድነት ሲወርዱ አስረክበዋታል፤ ትውልዱ ይህ እንደሚሆን ቢያውቅ ኖሮ ከዚህ ቀድሞ ባስወጣቸውም ነበር ነው ያሉት ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል፡፡ ይህንን አንድነት ለመጠበቅ ሁለት ዐብይት ሥራዎች ይጠብቁናል ብለዋል፡፡

የመጀመሪያው ❝እነርሱን ቀርቶ እነርሱን መሰል ቡድን በኢትዮጵያ ምድር ዳግም እንዳይበቅል መሥራት ይገባል❞ ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ነጮችን ከምንስብበት የኢንቨስትመንት እንክብካቤና አማራጭ በተለየ የአንዱ ክልል ባለሃብት ወደ ሌሎች ክልሎች ሄዶ የሚያለማበት መንገድ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ባይ ናቸው፡፡

እንደ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ማብራሪያ ምናልባትም ከውጭ የሚመጡ ባለሃብቶች ለችግራችን ደራሽ እና ለክፍተታችን ቀናሽ ገንዘብ ይዘው ይመጡ ይሆናል፤ የአንድ ክልል ባለሃብት ሌላ ክልል ሄዶ ሲያለማ ግን ከገንዘብ ባሻገር ወንድማማችነትን ይዞ ይመለሳል ነው ያሉት፡፡ በመሆኑም ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎች፣ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት እና ወጣቶች ለዘመናት ጠፍቶ የቆየውን እና አሁን ፍንጩ የተገኘውን ኢትዮጵያዊ አንድነት በጽኑ መሰረት ላይ በማቆም መትጋት ግድ ይላቸዋል ብለዋል፡፡ ከሀገራዊ አንድነት በኋላ ብሔራዊ ጥቅምን እና ሀገራዊ እድገትን ለማምጣት የሚኬደው ጉዞ ያን ያክል አድካሚ አይሆንም ነው ያሉት፡፡

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

መስከረም 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ)

mekonen 2
Previous Story

 ከውሸታም  ሰው  ና  ቡድን  ጋር  መደራደር  አይቻልም – መኮንን  ሻውል  ወልደጊዮርጊስ

Next Story

US Air Force: Why It’s The Best

Latest from Same Tags

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ

አረንጓዴ ልብ፣ ጥቁር ልብ፣ ሰይጣናዊ መንፈስ!

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) (መስከረም 21፣ 2017) October1,  2024) በጀርመን፣ በፍራንክፈርት አማይን በሚባል የታወቀ የፋይናንስና የባንክ ከተማ በወጣት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና ሰራተኞች የተቋቋመ አረንጓዴ ልብ(Green Heart) የመረዳጃ፣ የባህልና ከዚህም በመሆን
1967-74: Ethiopia's Student Movement

የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴና የ1966ቱ ሕዝባዊ አብዮት ዋዜማ – ፫ በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)

(ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደጻፈው) የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ እ.ኤ.አ. ከ 1950-1975 ‹‹… ጭንቅ ብሎኛል ኢትዮጵያዊ ማን ነው? ወጣት ሽማግሌው አገር ሲጠየቅ፤ አንዱ ጐጃም ነኝ ሲል ሌላው በጌምድር፤ አንዱ ኤርትራ ሲል ሌላው ተጉለት፤ አንዱ መንዝ ነኝ ሲል ሌላው ጋሙ ጐፋ፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ ባይ ብፈልገው ጠፋ፤ እስቲ አዋቂዎች እናንተ ንገሩኝ፤ እኔን ያስጨነቀው ኢትዮጵያዊው ማን ነው…?!››   (በ1950ዎቹ በዛን ጊዜው ቀ.ኃ.ሥ ዩኒቨርሲቲ

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ! – ማላጅ

ኢትዮጵያ ….ኢትዮጵያ እያለ በቃላት  የሚጠሩት ዕልፍ አዕላፍ ናቸዉ ትናትም ኢትዮጵያ ሲሉ በልባቸዉ የጥላቻ እና የጥፋት ቋጠሮ ሸክፈዉ ለዉድቀቷ ከዉስጥ እና ከዉጭ ጠላት ጋር ህብረት
Go toTop

Don't Miss