ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ሰብሳቢነት በተካሄደው “ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ ኢኒሼቲቭ” ጉባኤ ተሳትፈዋል

August 27, 2021

240802192 2073252532826084 4520380480329365644 n

የጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ዛሬ ከሰዓት በጠሩት የጂ-20 ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ የተሰኘ ጉባዔ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበይነ መረብ በመታገዝ ተሳትፈዋል።
“ለንግድ እና ለኢንቨስትመንት ማዕቀፋዊ ሁኔታዎች” በሚል ርዕስ የሚካሄደው ጉባዔ የስምምነቱ ፈራሚ የሆኑ ሀገራት ተጨማሪ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እንዲያገኙ በሚያስችል ሁኔታ ማዕቀፋዊ ሁኔታዎችን ወደ ቀጣይ ርምጃዎች ለመውሰድ የታለመ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር፣ ለሙዐለ ነዋይ ፍሰት ምቹ ነባራዊ ሁኔታ እንዲኖር ለማስቻል በኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አማካኝነት ማክሮ ኢኮኖሚያ፣ መዋቅር እና የዘርፍ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን እንደገለጹ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
(ኢ.ፕ.ድ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

news the future of ethiopia is at stake un chief
Previous Story

ለቸኮለ! ዓርብ ነሐሴ 21/2013 ዓ.ም የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች

240761225 2072947932856544 3515864049048125032 n
Next Story

“እናንየን ድው አደረጋት” በእናቱና አባቱ አስከሬን መካከል በደም ተጨማልቆ የተገኘው የሁለት አመት ህጻን

Go toTop