በአፋር የጁንታው አንድ ክፍለ ጦር ተደምስሷል!!!!!

August 9, 2021

235902644 4181648611882786 9219797526045594648 n

ዛሬ ነሐሴ 3/2013 ዓ.ም በአፋር ግንባር እጅግ ታላቅ ድል እየተመዘገበ ነው!!!!! ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ እየተካሄደ ባለው መጠነ ሰፊ ጥቃት ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን እና አናብስቶቹ የአፋር ልዩ ኃይላችን በጁንታው ተይዘው የነበሩ ቦታዎችን በአስደናቂ ጀብዱ እያፀዱ ይገኛል!!!!! በከፍተኛ እልህ እና ወኔ እየተዋደቀ የሚገኘው ጀግናው የአፋር ህዝባችንም ትልቅ ክብር ይገባዋል!!!!

ጁንታው በአፋር ህዝባችን ላይ ያደረሰው አሰቃቂ ግፍ በተለይ በጋሊኮማ መጠለያ ጣቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን የአፋር ህፃናትን እናቶችን እና አዛውንቶችን መጨፍጨፉን ተከትሎ መላው የአፋር ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ : የታጠቀም ያልታጠቀም : ፍየል ጠባቂው: የተማረው: ወንድ ሴት ሳይል ሁሉም የህልውና ዘመቻውን ተቀላቅለው በጊሌ እና በገጀራ ጭምር የጠላትን አንገት እየቀሉ ታንክ መማረካቸውን ወደፊት ታሪክ በደማቁ ይዘግበዋል!!!! የአፋሩ ጀግና ሃመዱ የጁንታውን ታንክ ተኮሽ ታንኩ ላይ በመውጣት በጊሌ አርዶታል!!!! የአፋር አባት በጁንታው የተገደለበትን ልጁን ሳያነሳ በቀጥታ ጠላትን ለመበቀል ወደ ፍልሚያ ገብቷል!!!!! የአፋር እናት የተገደለባትን ልጇን ከመቅበር ይልቅ የልጇን ገዳይ ለመግደል እንባዋን ዋጥ አድርጋ ዘምታለች!!!!! ሁሉም ወደፊት ብቻ ይገሰግሳል!!!!ብዙ የሚነገሩ አፈ ታሪክ የሚመስሉ አንፀባራቂ ተጨባጭ ታሪኮች እየተመዘገቡ ነው!!!!!

235810984 4181630388551275 3984442519483811112 n

የህዝብ ማዕበል አስነስቶ የመጣን ጠላት የታጠቀ ሰራዊትን ብቻ በማሰማራት ሳይሆን በእንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ የህዝብ ማዕበል ነው መመከት: መቀልበስ ብሎም መልሶ ማጥቃት እና ማፅዳት የሚቻለው የሚለውን ሃቅ የአፋር ህዝብ በተግባር አረጋግጧል!!!! ይህ ዘመቻ የህልውና ዘመቻ እንጅ ቀበሌን ወይም ከተማን የመያዝ አለያም የማስለቀቅ የዥዋዥዌ ጨዋታ አይደለም!!!! የህልውና ዘመቻ ማለት ህልውናህን ሊያጠፋ ቀዬህ ድረስ የመጣን አራጅ ጠላት መክተህ እና ቀልብሰህ ህላዌህን ማረጋገጥ ማለት ነው በትንሹ!!!! ምርጫው ሁለት ነው!!!! ወይ ህልውናህን ማረጋገጥ አለያም መጥፋት ነው!!!! ሌላ ሶስተኛ ምርጫ የለም!!!! ይህን የተረዳው ጀግናው የአፋር ህዝብ ትንሽ ትልቅ ሳይል ሰበብ ሳያበዛ ህልውናውን ለማስቀጠል በተግባር እየተፋለመ ነው!!!! ለዚህ ደግሞ የአፋር አመራሮች ህዝባቸውን ሞቢላይዝ በማድረግ ረገድ የተጫወቱት ታሪካዊ ሚና በቃላት የሚገለፅ አይደለም!!!!! ሌሎች አመራሮችም ከዚህ ሊማሩ ይገባል!!!!

235438460 4181630225217958 6745313618171901318 n

ጀግናው መከላከያችን እና የአፋር ልዩ ኃይላችን ከጫፍ እስከ ጫፍ የተነቃነቀውን መላውን የአፋር ህዝብ ደጀን በማድረግ እነሆ በዛሬው ዕለት ሃያል ጀብዱ እየፈፀሙ እና ጠላትን አይቀጡት ቅጣት እየቀጡ ጣፋጭ ድልን እያጣጣሙ ይገኛል!!!! ጁንታው ከባድ መሳሪያዎቹን ተክሎ እና ያለውን ሃይል አሰልፎ ወደ ጭፍራ እሻገራለሁ ብሎ የሃይል ማዕከል አድርጎት የነበረችው ኡዋ ከተማ ከማለዳ ጀምሮ በተካሄደው ጦርነት ጁንታው የሰራዊታችንን እሳት ክንድ መቋቋም አቅቶት ኡዋን ለቅቆ ወደ አውራ በመሸሽ ላይ ይገኛል!!!!

በደረሰኝ ተጨባጭ መረጃ “ኡዋ” ላይ
= የጁንታው አንድ ሙሉ ክፍለ ጦር ከጥቅም ውጭ ሆኗል!!!!
= የሙት ቁጥር ጧት ከተመዘገበው ከ 300 ወደ 650 ተጠግቷል!!!!
= 265 ቁስለኛ እና 47 ምርኮኛ ተመዝግቧል!!!
የጁንታው 265 ቁስለኛ እና 47 ምርኮኛ በሰራዊታችን እጅ ገብቷል!!!! ይህ በተጨባጭ የተቆጠረው ነው!!!! በየጊዜው ሊጨምር እንደሚችል ይጠበቃል!!!!
= የቀረው ሃይል እግሬን አውጭኝ ብሎ በስምንት ተሳቢ ወደ አውራ ሸሽቷል!!!! የአየር ፀባዩ ለ air strike ብዙም አመች እንዳልነበር ተነግሯል!!! ይህ በእንዲህ እንዳለ ጁንታው ኡዋ ከተማን ለቅቆ ሲወጣ ከተማዋን በፈንጅ እንዳጠረ ሰራዊታችን ባለው ጠንካራ ወታደራዊ መረጃ እና ደህንነት አስቀድሞ በመገንዘቡ ከጁንታው ነፃ የሆነችውን ከተማዋን ከመቆጣጠር ይልቅ በጥልቅ ወታደራዊ ጥበብ ሌሎች (እዚህ የማይገለፁ) ወታደራዊ ስራዎችን በአስደናቂ ሁኔታ እየሰራ ነው!!!! በተጎዳኝ የፈንጅ አምካኞቻችን ስራም በዝቷል!!!!
ለጀግናው መከላከያችን ለጀግናው የአፋር ልዩ ኃይል እና ለበርሃ አናብስቱ የአፋር ህዝባችን እና አመራሮች ባርኔጣችንን አውልቀን ከፍ አድርገናል!!!!! ሰራዊት እና ህዝብ ትክክለኛ መሪ ሲያገኝ ውጤቱ እንደዚህ ነው!!!!! ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን!!!!! በሁሉም አቅጣጫ ያሉ ዘመቻዎችም እየተስተካከሉና ክፍተቶች እየተሞሉ በቀናት ውስጥ ድል በድል እንደምንሆን የአፋር ግንባር ህያው ምስክር ነው!!!!! በተናጥል ድል የምንረካ አለያም በትንሽ ክፍተት የምንደነግጥ እርብትብቶች አይደለንም!!!! ትልቁን ስዕል ማየት ግድ ነው!!!! ይልቅ ከሰራዊቱ ጎን እንቁም!!!! የጠላትን የፕሮፖጋንዳ ውዥንብር እንድፈቅ!!!! ካልገባን ዝም እንበል!!!! ካሳሰበን እንፀልይ!!!!! እውነት እላችኃለሁ በመጨረሻ ኢትዮጵያ ማሸነፏ ቅንጣት ጥርጥር የለውም!!!!!
EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published.

231224439 573354777452638 1388178489852320492 n
Previous Story

የአማራ ክልል መንግስት ህወሃት ወልዲያ ላይ በተኮሰው ከባድ መሳሪያ በንጹሀን ላይ ጉዳት ማድረሱን ገለጸ

Next Story

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተላለፈ መልዕክትና ሀገራዊ ጥሪ!

Go toTop