ይህ ፎቶ የዛሬ የጋይንት ውሎ ነው!
የጋይንት ህዝብ የጨጨሆ ላይ መንገዱን (የወሎ፣ ትግራይ፣ ጎንደር መገናኛ ዋና መንገድ) ዘግቷል።2008 ላይ ወያኔ አፈር ደሜ የበላው እዚህ ነው።ዘንድሮም ሚሊሻው “ተመለሱ ተብለናል” በሚል ሲመጣ ውስጣችሁ ይፈተሽ ጠላት ተመሳስሎ ይኖራል በሚል መንገድ ዘግቷል።
አንፈተሽም፣ ትፈተሻላችሁ በሚልም ግጭት ነበር።(ያደረጉት ትክክል ነው ስህተት ነው ማለት አልችልም)።
ሆኖም አንድ ሀቅ ነግሮናል።ህዝብ ቢያንስ አንድ ትልቅ ጉልበት አለው።መንገድ በመዝጋት ጠላትን መግቢያ መውጫ ማሳጣት እንደሚቻል።እነዚህ የእኛ ሚኒሻዎች ጠላት አይደሉም።ግን በተሳሳተ መረጃ እነርሱም የተሳሳቱ ይመስለኛል።ህዝቡም ጥርጣሬ ስላደረበት መንገድ ዘጋ።ትንሽ ቆይቶ ምግብ አብልቶ አብሮ ጠላትን እንደሚዋጋ እግመታለሁ።
ላሊበላ አንድ ጥይት ሳይጮህ ወያኔ ሲገባ ጣት ከመጠቋቆም ጠላት ሊመጣ ይችላል ብሎ ህዝብን ማስተባበር የተሻለ መፍትሄ ነበር።
ገዳይ ሲመጣብህ ለመሞት መዘጋጀት ነው።እከሌ ሸሸ፣ እከሌ እንዲህ ሆኖ ማለት አይሰራም።
ጅብ ከሚበላህ ገድለው ተቀደስ!!!
ጋይንት ጨጨሆን ብቻ ሳይሆን ሌላ መንገዶችንም ዛሬና ነገ እንደሚዘጋቸው ወይም እንደዘጋቸው አምናለሁ።
ጠላት በላሊበላ ቀለበት ውስጥ ገብቷል። በቅርቡ ቀብሩ ይፈፀማል!!
Ayalew Menber