ሀይለማርያም <ያገር መሪ>
ለሆድህ ፙች ለሆድህ ኑዋሪ፤
የሰውነት ክብርህን ሻጭ
ለ<ስም> ዝና ፍርፋሪ፤
ሀፍረት የለህ፤ ጸጸት የለህ
አንት በቁም ቀባጣሪ፤
አኵዋንህ አድራጎትሕ
ወዳጅ ዘመድ አሳፋሪ፤
ሀይለ መለስ፤ ሀይለ ጸጋይ
ሀይለ ስዩም፤ ሀይለ አባይ
ሀይለ አዜብ፤ ሀይለ ድንጋይ
አስመስሎ ተናጋሪ
በሬ ወለደ ቃል አቀባይ
የ<ፐፔት ሸው> መሪ ተዋናይ።
አኩዋንህ፤ ንግግርህ
የኣጆችህ ንቅናቄ
የጣቶህ አዘራዘር
ጠፍጣፊህን፥ ጌታ መሳይ፤
ባታውቅ እንጂ፥ ምን ታደርገው
ራስን ትቶ፥ ሌላ መምሰል
ከራስ ማጥፋት፥ ከራስ መግደል
ተመስልዋል በፈላስፋው።
እንግዲያማ ዘመዶችህ
ዕርም ያውጡልህ፥
ሙሾ ያውርዱ
ሀይለማርያም ራሱን ገድልዋል
በቁም ቢኖር፥ በቁም ሞትዋል
ብለው ያንቡ፥ ይጩሁልህ
ወዮ ልጄ፥ ወዮ ወንድሜ
ወዮ አባቴ፥ ወዮ አጎቴ
ብለው ያልቅሱ፥ ይጩሁልህ፤
ደረት ይምቱ፥ ይደልቁ
አጥንታቸውን እስኪያደቁ፤
ይንደርደሩ፥ ይፎክሩ
ይዝለሉና፥ ይገልበጡ
ባገሬው ደንብ እርምም ያውጡ።
ሳትሞት በቁም ሞተሃልና
ለሆድ አድረህ፥ ለወንበዴ
ለባንድና አገር በታኝ
ሆነህ ሎሌ ገብተሃልና፤
አዎን፥
ሀይለ መለስ፥ ሀይለ ጸጋይ
ሀይለ ስዩም፥ ሀይለ አባይ
ሀይለ አዜብ፥ ሀይለ ድንጋይ
አስመስሎ ተናጋሪ
በሬ ወለደ፥ ቃል አቀባይ
የ<ፐፔት ሾው> መሪ ተዋናይ፤
ዘመዶችህ ዕርም ያውጡልህ
እዬዬውን ያቅልጡልህ
ይጩሁና ያቅራሩልህ፤
ቤተ ሃይማኖት ወዳጆችህ
ይዘምሩ፥ ይጸልዩ
አያውቅምና የሚያረገውን
ይቅር በለው፥ ይበሉልህ።
ከሰለሞን ታረቀኝ
ህዳር 2006