ማስተዋል ከአልተቻለ ገና ብዙ ነገር አለብን! – ሰርፀ ደስታ

October 24, 2019

ነጻ የነበረውን ሕዝብ ነጻ እናወጣሀለን ብለው ይሄው ዛሬ የአስተሳሰብ ባርነት ውስጥ ከተው ዋና መከላያ መሣሪያቸው አድርገውታል፡፡ አማራን ጨቋኝ በማድረግ ሌላውን ተጨቋኝ በማድረግ አባቶቹና አያቶቹ የማያውቁትን ጭቆና ይሄ በ50ዓመት የጥላቻና ዘረኝነት መርዝ የተሞላ ትውልድ በባርነት እየማቀቀ ይገኛል፡፡ አዝናለሁ በጨቋኝነት ለዘመናት ገዛ የተባለውም ይሄው አሁን በተጨቋኝነት ባርነት ለመቀላቀል እየተንደረደረ ይመስላል፡፡ አገር፣ሕዝብ የሚባል ነገር ማሰብ ይቅርና እየገደሉት ያሉትን ጠላቶቹን እንኳን መለየት ተስኖት ለጠላቶቹ ዋና መሣሪያ ሆኗል፡፡ በተለይም የኦሮሞን ሕዝብ እንዴት የኢትዮጵያ ጠላቶች ከኢትዮጵያዊነት አውጥተው  እየተጠቀሙበት እንደሆነ ለማስተዋል ከሊቅ እስከደቂቅ ያሉ በርካቶች ዛሬ ለእነሱ ዲሞክራሲ ማለት ሌላውን መጥላት በተለይም ጠላቶቹ በአጠመቁት የጸረ አማራ ንግርት መኖር አንደሆነ እያየን ነው፡፡ ኦሮሚያ የሚባለውን ክልል እንዲመራ የተሰየመው ዋናው ሳይቀር ወያኔና ደብተራዎቿ በነገሩት የነፍጠኛ ትርክት ከ150 ዓመት በፊት ሆነ እያለ ወላጆቹና አያቶቹ የማያውቁትን ታሪክና ስጋት ዛሬ እሱ ይባንንበታል፡፡ አዝናለሁ! አሁን ደግሞ እነዚያው ኦሮሞንና ሌላውንም ተጨቁነሀል እያሉ 27ዓመት  ሲገድሉትና ሲያዋርዱት የነበሩት ቀጥረውት ኦሮሞን በጥላቻና ዘረኝነት ባርነት አስሮ እንዲያገለግላቸው ሲጠቀሙበት የነበረን ግለሰብ ዛሬ ብዙ ኦሮሞ ወደ ማምለክ የጀመረው አይነት ሆኖ እናየዋለን፡፡ አዝናለሁ!  የኦሮሞን ወጣት ቄሮ በሚል ማጃጃል ወደ ለየለት የሽብር አስተሳሰብ ባርነት እየጨመሩት እንደሆነ ታዘቡ፡፡ ቄሮ ማለት ወጣት ማለት ነው ይሉሀል፡፡ ጉዳዩ ከቃሉ ላይ አደለም፡፡ አልሸባብ ማለት እንደወረደ በአረብኛ ወጣት ማለት ነው፡፡ የኦሮሞ ፖለቲካ ከየት ተነስቶ ወዴት እንደሚሄድ የቱንም ያህል ቢገባኝም ዋናውን ጉዳይ በዚህ ሚዲያ መናገር አልፈልግም፡፡ ጉዳዩ ግን አደገኛ ሀይማኖታዊ ሴራ እንደሆነ ከድሮም ጀምሮ አውቀዋለሁ፡፡  የኦሮሞ ወጣት ራሱን ቆም ብሎ ሊያስተውል ይገባዋል፡፡ ከሕግና ሥርዓት ውጭ የሚቀሰቅሱትን ከአልነቃባቸው የእነሱ የንግድ ዕቃ እያደረጉት ይቀጥላሉ፡፡

ጨቋኝ የተባለው አማራ ዛሬ ከኦሮሞ ቀጥሎ ዋና ሥርዓተ አልበኛ ወጣት እየወጣበት ያለ ነው፡፡ አማራና ቅማንት ሲጀምር በምን እራሳቸውን እንደሚለዩ አይገባኝም፡፡ በሚለዩበት ይለዩ ግን አሁን በጠላት በሚሴርላቸው መረብ እነሱ ይጫረሳሉ፡፡ በዚህ ሴራ በኦሮሞ ዋና የኦሮሞ የነጻት ተዋናይ ነን የሚሉትና ኦሮሞንና ሌላውንም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲገድልና ሲዘርፍ የኖረው ቡድን በቅንጅት መስራታቸው ሳይደንቅ በኦሮሞ የዘረኝነትና ጥላቻ ባርነት የወደቀው ሌላው ሁሉ በዚህ አጋዥ ነበር፡፡ ከታማኝ በየነ በላይ ኦሮሞ ስለቅማንት ሕዝብ አሳቢ ሆኖ ታማኝ ተብዬው የት አለ ዛሬ ቅማንት ሲገደል በሚል መርዛቸውን በሰፊው ሲረጩ ሰንብተዋል፡፡ አማራ ነኝ የሚለው ወጣት በስሜት መደንፋትና በሌላው ላይ ጥላቻን ማሰራጨት አሸናፊነት እየመሰለው ነው፡፡ አጀንዳ ይፈጥሩለታል፡፡ ወልቀይት የአማራ ነው ራያ ወደ አማራ ይመለስ ምናምን አስተውሉት፡፡ ሲጀምር ወልቀይትም በሉት ራያ ወይም ሌላ ማን ለአማራ ሰጠው የትግሬስ ማን አረገው፡፡ ሕግና ፍትህ ሰፍኖ ሁሉም በሚኖረበት ቦታ በሰላምና በስርዓት እንዲኖር እንጂ አንዱን አሳዶ ሌላውን ለማስፈርማ ወያኔ ከአደረገቸው ምን የተለየ ሆኖ፡፡ ይህን አስተውል

ኢትዮጵያውያን ሆይ አስተውሉ፡፡ ዛሬ ነገሮች ብሰውብኝ እንጂ መናገርም አልፍልኩም ነበር፡፡ 50 ዓመት በጣላቻና ዘረኝነት የተጎዳ ማህበረሰብ ዛሬም ድረስ በሰላም መኖሩ የእግዚአብሔር ጥበቃ ኖሮ ነው፡፡ ለአብይና በመንግስት ስልጣን ላይ ላላችሁ በሙሉ፡፡ እጅግ አዝናለሁ! በማጭበርበር ብዙም የምትዘልቁት አይመስለኝም! አንዴ ነገሮች ግን ከቁጥጥር ውጭ ከሆኑ ለእናንትም አይቀርም፡፡ ምን አልባት በዛ ልክ ከከፋ ማምለጫ አለን ብላችሁ አስባችሁ ይሆናለ፡፡ ይሄ አይሆንም! ፍርድ ከላይ ነውና፡፡ በሠላማዊ መንገድ ፍትህ የሚጠይቁ ዜጎች በአሸባሪነት እየታፈሱ እስር ቤት ገብተዋል አሸባሪዎችና ይበልጠውንም የሌላ አገር ዜጎች ግን አገርንና ሕዝብን ግጭትና ሽብር እየፈጠሩ ለእነሱ ጥበቃ እየተደረገላቸው ይኖራሉ፡፡ ይህ የሆነው አብይ አሜሪካ መጥቶ በሚኒሶታ በተደረገ ውል እንደሆነ እንታዘባለን፡፡ ከዚህ ውጭ ግን ዜጎች ራሳቸውን ለመጠበቅ ሲሉ የእራሳቸውን እርምጃ ሁኔታዎች ሲከፉባቸው ሊወስዱ እንደሚችሉ ግልጽ ነው፡፡ አሁንም የምናየው ይሄንኑ ነው፡፡ በመስቀል በዓል እለት ሰውን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ጥለት ያለው ልብስ አትልበሱ፣ ባንዲራ ትያዙ ብሎ በሰላሙ ቀን የሽብር አዋጅ ያወጀው ማን ነው፡፡ ደብረ ዘይት መስቀል እንዳይከበር የከለከለው ማን ነው፡፡ በኦሮሚያ አንዳንድ ቦታዎች ሀይማኖታዊ በዓል አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ምልክት ያለበት ማንኛውንም ነገር መያዝ አትችሉም እያለ ሕዝብን ለቁጣና ለአጽ እያነሳሳ ያለው ማን ነው፡፡ በዛሬው እለት በዚህ ምክነያት ትልቅ ረብሻ እንደተፈጠረ እናውቃለን፡፡ አሁን ሕዝብ መሮታል! አዝናለሁ፡፡

አረብኛ የምትችሉ ኢትዮጵያውያን ሆይ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ እባካችሁ ተርጉሙና ከኢትዮጵያ ፖለቲካ መሠል ሴራ ጀርባ ማን እንዳለ ለግንዛቤ ለሕዝቡ አድርሱ፡፡ ይህ ግለሰብ ኦሮሞ፣ ሙስሊም አማራ፣ ኢስራኤል  ምናምን ይላል ምን እያለ ነው

https://youtu.be/rXipm_tcDGo

ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

Previous Story

“ትህነግ”: በሞተ ርዕዮተ-ዓለም የሚመራ፣ ለውጥን የሚፈራ ድርጅት – ስዩም ተሾመ

Next Story

ጦቢያ ግጥምን በጃዝ #98-11 -ተስፋሁን ከበደ- ”ግድግዳውን አፍርሰን ድልድይ እንስራለን” አሉ .. – Tesfahun kebede [Arts TV World]

Go toTop