“አዲስ አበባን እንደ ባግዳድ ፤ አማራንም እንደ ኩርድ ” የእነ ታከለ ኡማ እቅድ (ፈለገ_ግዮን)

October 22, 2019

1. የኢሊሌ ብርጌድ ምንድን ነው?

በታከለ ኡማ የተመሰረተው #የኢሊሌ_ብርጌድ ምን እየፈፀመ ነው? ስምሪቱንስ ከየት ይወስዳል? የፋይናንስ ምንጩስ? የፀጥታ ሃይሉ ድጋፍስ? … የሚለውን እንይ። ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ወንጀል በመፈፀም አቻ የማይገኝላቸውን መንጋዎች በማሰባሰብ “ፎሌ” የሚል ስያሜ ያለው ወንጀለኛ ማህበር በአዲስ አበባ ተመስርቷል። ፎሌ በይፋ ስሙ ሰላማዊ የወጣት አደረጃጀት ነው – ተግባሩ ደግሞ የሽብር። ይሄ የኢሊሌ ብርጌድ ስምሪት የሚሰጠው ኢሊሌ ሆቴል ሲሆን ትዕዛዝ የሚቀበለውና የፋይናንስ ምንጩን የሚያገኘው ደግሞ ከታከለ ኡማ አስተዳደር ነው።

2. የማፍያ ቡድኑ የስምሪት ቀጠና

ይሄው ማፍያ ቡድን የስምሪት ቀጠና ተሰጥቶታል። አንደኛው ከአዲስ አበባ ነው። በአዲስ አበባ የሚከናወኑ የትኛውም አይነት ከታከለ ኡማ በተፃራሪ የሆኑ ስብሰባዎችን በጉልበት ይበትናል። እቅዱም አዲስ አበባን የኦሮሞ ማድረግ ሲሆን፣ ይሄ ካልተሳካ ግን ልክ እንደ ባግዳድ በአንድ ጀንበር ማፈራረስ ነው። የአማራና የኢትዮጵያ የመሰለውንም እየተከታተለ ያጠፋል።

ሌላው የማፍያ ቡድኑ ቀጠና ከሚሴ ነው። ከአዲስ አበባ ከሚሴ ያለከልካይ በመንግስት በጀት ይንቀሳቀሳል። በዚህም ወሎ የኦሮሞ ነው የሚል አላማ አንግቦ ይሰራል። ያለ ከልካይም በዚህ መስመር እየተንቀሳቀሰ ወንጀል ይፈፅማል። ከዚሁ ጋር ተያይዞም የሸዋ ኦሮሞ ሴንትሜንቱ የኦሮሞ አይደለም የሚል አንድምታ ወስደዋል። በዚህም ከአዲስ አበባ ጎጃም መስመር፣ ከአዲስ አበባ ደብረ ብርሃን መስመር ያሉትን አካባቢዎች መቆጣጠር ነው። በዚህ መስመርም የአካባቢው ሰው ከየት እንደመጡ የማያውቃቸው ወጣቶች መንገድ ይዘጋሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ያስፈራራሉም።

3. የወንጀለኛው ቡድን መሪ ማነው?

ይሄ በታከለ ኡማ የተደራጀው የመንጋ አደረጃጀት የራሱ መዋቅርና መሪ አለው። የቡድኑ መሪም ወጣት #አትናቲዎስ_ቢቂላ ይባላል። ይሄ ልጅ በመደበኛ ስራው የቦሌ ክ/ከተማ የኦሮሞ ወጣት ማህበር ሰብሳቢ ነው። በታከለ ኡማ ትዕዛዝ ደግሞ የፎሌ ሃላፊ ሆኗል። ይሄ ወጣት ከከተማ አስተዳደሩ በጀት RAVA4 መኪና ተሰጥቶታል። ሁለት የግል ጠባቂዎችም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተመድቦለታል። በአጠቃላይ የማፍያ ቡድኑ አመራሮች አዲስ አበባን በስም ብቻ የሚያውቁ የሌላ አካባቢ ልጆች ናቸው።

4. የማፍያ ቡድኑ አባላትና የሚጠቀምበት ሽፋን

ይሄው የማፍያ ቡድን አባላቱም በዋናነት ከሌሎች የኦሮሚያ አካባቢ የመጡ ናቸው። ቀሪዎቹ ደግሞ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን እና ተማሪዎች፣ በዝውውር ስም ከሌላ አካባቢ የመጡ የመንግስት ሰራተኛዎች … ወዘተ ናቸው።

የሽብር ቡድኑ ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀስ እንደ ሽፋን የሚይዘው “የደህንነት መታወቂያ” ነው። የደህንነት ሰራተኞች ነን እያሉና መታወቂያም እያሳዩ የፈለጉትን እንዲፈፅሙ ከታከለ ኡማ ትዕዛዝ ወርዶላቸዋል። የደህንነት ተቋሙና የአዲስ አበባ ፖሊስም ትብብርና ድጋፍ ያደርግላቸዋል።

5. አማራ የለም

አዲስ አበባንም ሆነ ወሎን የኦሮሞ የማድረግ አላማቸው እንቅፋት ሊሆን ይችላል ያሉት ደግሞ በዋናነት አማራን ነው። አማራን አንገት ማስደፋት ብቻም ሳይሆን ማጥፋት የሚል እቅድም ከታከለ ኡማ ተቀብለዋል። በእርግጥ እነ ጃዋር፣ ፀጋዬ እና ህዝቅኤልም የዚህ እኩይ ተግባር መስራችም፣ ደጋፊም ናቸው። ያም ሆኖ ታከለ ኡማ ይህንን እቅድ ተቋማዊ መሆነ መንገድ በመምራቱ ነው ቀተለየ መንገድ ማየት የሚያስፈልገው። በዚህም በተለይ በፊት በፊት አማራ የለም የሚሉት የሌሎች ብሄር ተወላጆችና ከራሱ ከአማራው የወጡ ማህይም ምሁራን ሲሆኑ፣ አሁን ግን አማራ የለም የሚሉት እነዚህ የመንጋ አስተሳሰብ ተሻካሚዎች ሆነው ታገኟቸዋላችሁ። በዚህም አማራን ልክ እንደ “ኩርዶች” ሀገር አልባ የማድረግ እቅድ ይዘው እየሰሩ ነው።

6. የአዲስ አበባ ፈተና – ከምርጫ ውጤት ማግስት

በ2012 ምርጫ በጉልበትም፣ በስርቆትም የታከለ ኡማ አስተዳደር እንዲያሸንፍ ማድረግ እቅዳቸው ነው። ይሄ ካልሆነ የታከለ ኡማ ቡድን ይበተናል፣ የሚሰፈርለት ድርጎም ይቆማል። በመሆኑም በዚህ ምርጫ ታከለ ኡማ እንዲያሸንፍ ይሰራሉ። በዚህ ሁሉ አፈና የታከለ ኡማ አስተዳደር ከተሸነፈ ደግሞ ሌሎች አማራጭ የሽብር እቅዶች ተዘጋጅተዋል። አንዱ በሁሉም አቅጣጫውች ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ መንገዶችን መዝጋት፣ የውሃ መስመርችን መቁረጥ፣ የመብራት ምስሶዎችንም መቆራረጥ ነው። ሌላው ደግሞ በዚሁ በከተማው ውስጥ መሳሪያና ፈንጅ በመጠቀም ሽብር መስራት ነው። አዲስ አበባ ወይ የኦሮሞ፣ ወይ እንደ ባግዳድ በፍርስራሽ ማልበስ የሚል አላማን አንግበዋል።

7. የኢሊሌ ብርጌድ ሁለቱ ክንፎች

የኢሊሌ ብርጌድ ሁለት ክንፎች አሉት። አንደኛው ከላይ የተጠቀሰው የሽብር ቡድን ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ የሰላ ብዕር ያላቸውን ጦማሮች፣ ከያንያን፣ ገጣሚያን፣ ዘፋኞች፣ ፀሃፊዎች … በገንዘብ በመግዛት ታከለን እንዲያሞግሱ ማድረግ ነው። በዚህም ለጊዜው አንዳንድ ሆድ አደር ጦማርያንን በእጁ አስገብቷል። ከውጭም፣ ከሀገር ውስጥም ያሉ ጦማሪዎች ናቸው በእቅድ የተያዙትም፣ አሁን ይህንን ተግባር እየፈፀሙለት ያሉትም።

8. የመደበኛ ሚዲያዎችን እጅ ማስገባት

የብሮድካስት ዜና ኤዲተሮች፣ የኦንላይን ሚዲያ አዘጋጆች እና የኘሪንቲንግ ሚዲያ ኤዲተሮች በታከለ ኡማ የተያዙ ናቸው። የእለታዊ፣ ሳምንታዊ እና ወርሃዊ የዜና ሽፋናቸው እየታየም በታከለ ኡማ አበል ይቆረጥላቸዋል። እንደየ አፈፃፀማቸውም ጠቀም ያለ ጉርሻ ይለቀቅላቸዋል። በዚህም ታከለ ኡማ ያደረጋት ጥቃቅን ተግባር ሳትቀር ዝርዝር ዜና ይሰራላታል። ሪፖርተርም ይመደብላታል።

9. መፍትሔ

ፈረንጆች የማይቀርን ጉዳይ inevitable ይለዋል። አማራም የማይቀር የህልውና ትግል ውስጥ ገብቷል። በመሰረቱ አማራ መከበቡን የእኛ ሰዎች ቀድመው ነግረውን ነበር። እኛ ግን መዳኛችንን ከማፈላለግ ይልቅ ምርጫችን መጠላለፍ ሆነ። ኦዴፓ ቄሮ የሚባልን መንጋ በህጋዊ አደረጃጀት ቀይሮ ፍላጎቱን በሃይል ያስተገብራል። እኛ ደግሞ ፋኖን በጠላትነት፣ ጀግኖቻችንን በመንደር ወጠጤነት፣ አንቂዎቻችንን ደግሞ በአክራሪነት ከሰን አሰረናቸዋሌ። እያሳደድናቸውና እየገደልናቸውም እንገኛለን።

በመሰረቱ የአማራ ጠላቱ ሆዳም አማራ መሆኑን ቀድመን ብንረዳም፣ ህዳሞችን ግን ከራሳችን ማውረድ አልቻልንም። ወይ ደግሞ አመለካከታቸውን ቀይረን፣ ተግባራቸውንና ምግባራቸውንም አድሰን አልተጠቀምንባቸውም። የሆነው ሆኖ ከዚያም ከዚህም የአማራ ጀግንች አሉን። እነዚህን አሰባስበን መፍትሔ ማስቀመጡም ለነገ የሚባል አዬደለም።

ዞሮ ዞሮ መፍትሄው መደራጀት ነው። ህግ፣ የህግ አካላት … መብቴን ያስከብርልኛል ብሎ ማሰብ ነዋህነት ነው። መዳኛችንን የምናገኘው በሃይላችን ብቻ ነው። ነገን በህይወት የምናገኘውም በመሰባሰብ ነው። የመጣብንን ደራሽ ጎርፍ የምንሻገረውም እጅ ለእጅ ተያይዘን እንጂ፣ ትክሻ ለትክሻ በመገፋፋት አይደለም። እንደራጅ፣ ህይወታችንን እናትርፍ!

#ፈለገ_ግዮን

Previous Story

የሕብር ሬዲዮ ጥቅምት 09 ቀን 2012 ዓ.ም. ፕሮግራም

Next Story

የዛቻ ጦርነት – ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም

Go toTop